የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የድኅረ-ምረቃ ትምህርት ቤት በ2014 የትምህርት ዘመን በመደበኛ፣ በማታ እና በሳምንት መጨረሻ መርሃ-ግብር መስፈርቱን የሚያሟሉ አዲስ አመልካቾችን ከዚህ በታች በተጠቀሱት የትምህርት መስኮች ተቀብሎ ማሠልጠን ይፈልጋል፡፡
ለምዝገባ የሚያስፈልጉ መረጃዎች
- ሙሉ የትምህርት መረጃ ኦርጅናልና ሁለት(2) ፎቶ ኮፒ እንዲሁም ሁለት(2) ጉርድ ፎቶግራፍ
- የአመልካቹን ጥንካሬና ባህሪ የሚገልጽ ከመ/ቤት ኃላፊ /ከቀድሞ መምህር/ የተጻፈ የድጋፍ ደብዳቤ /Recommendation Letter/
- በመንግሥት/በድርጅት ስፖንሰርነት ለሚማሩ በመሥሪያ ቤቱ/ በድርጅቱ ኃላፊ የሚፈረም/Sponsor hip Form/ ከዩቪርሲቲው ድረ-ገፅ www.amu.edu.et ማግኘት ይችላል፡፡
- የመመዝገቢያ ክፍያ የ100 ብር ደረሰኝ በመያዝ የማመልከቻ ቅጽ ከተማሪዎች ምዝገባና ቅበላ ክፍል ቢሮ ቁጥር 210፣ 211 እና ከዩቪርሲቲው ድረ-ገፅ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የማመልከቻ፣ የፈተና መስጫ፣ የውጤት ማሳወቂያ፣ የምዝገባ ጊዜና ቦታ
- የማመልከቻ ጊዜ፡- ከነሐሴ 06 - 30/2013 ዓ.ም
- የማመልከቻ ቦታ፡- የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት የተማሪዎች ምዝገባና ቅበላ ክፍል ቢሮ ቁጥር 210፣ 211 እና አዲስ አበባ ጉዳይ ማስፈፀሚያ ጽ/ቤት አራት ኪሎ ሮሚና ካፌ ጎን
- ለፈተና ያለፉ አመልካቾች ዝርዝር በውስጥ ማስታወቂያና በዩኒቪርሲቲው ድረ-ገጽ የሚገለጽበት መስከረም 05/2014 ዓ.ም
- የመግቢያ ፈተና የሚሰጥበት ቀን፡- መስከረም 12/2014 ዓ.ም፤
- ፈተና የሚሰጥበት ቦታ፡-
- የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት፣ የማኅበራዊ ሳይንስና ስነሰብ ኮሌጅ፣ የሕግ ት/ቤት፣ የስነ-ትምህርትና ስነ-ባህሪ ሳይንስ ት/ቤት እና የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ አመልካቾች በድኅረ-ምረቃ ት/ቤት ሕንፃ ዋና ግቢ
- የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ አመልካቾች በተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ዓባያ ካምፓስ
- የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ አመልካቾች በሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ነጭ ሣር ካምፓስ
- የግብርና ሳይንስ ኮሌጅ አመልካቾች በግብርና ሳይንስ ኮሌጅ ኩልፎ ካምፓስ ይሆናል፡፡
- የመግቢያ ፈተና ያለፉ አመልካቾችና የምዝገባ ጊዜ በቀጣይ የሚገለፅ ይሆናል፡፡
ማሳሰቢያ፡-
- ማንኛውም የመግቢያ ፈተና ያለፈ አመልካች ኦፊሻል ትራንስክሪፕት /Official Transcript/ ብቻል በምዝገባ ወቅት ካልሆነ በ60 ቀናት ውስጥ ካልቀረበ ዩኒቨርሲቲው የማያስተናግድ መሆኑን ከወዲሁ በጥብቅ ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡
- በአካል ቀርባችሁ ማመልከት ለማትችሉ አመልካቾች በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000021480502 የማይመለስ 100 ገቢ ያደረጋችሁበት ደረሰኝና ሙሉ የትምህርት ማስረጃችሁን ኮፒ/ስካን በማድረግ በኢ-ሜይል አድራሻችን
This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. ማመልከት ትችላላችሁ፡፡ - የትምህርት ፕሮግራሞች ዝርዝር በዩኒቨርሲቲው ዌብሳይት፣ ፌስቡክና ቴሌግራም ቻናል የተቀመጠ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
የአርባ ምንጭ ዩንቨርሲቲ ሬጅስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት