ሳውላ (ሰኔ 21/2018 .) የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሳውላ ካምፓስ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሠለጠናቸውን 121 9 ባች ተማሪዎቹን ዛሬ ሰኔ 20 ቀን 2018 . በደማቅ ሁኔታ አስመርቋል። ከተመራቂዎቹ መካከል 109 በመጀመሪያ ዲግሪ መርሐ ግብር የተመረቁ ሲሆን፣ ቀሪዎቹ 12 ተማሪዎች ደግሞ በማስተርስ ፕሮግራም ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ናቸው። ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

በበዓሉ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት አቶ ቦጋለ ፈይሳ ባደረጉት ንግግር፣ ለተመራቂ ተማሪዎች፣ ለወላጆችና ለመላው የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት አስተላልፈዋል። አቶ ቦጋለ ፈይሳ ተመራቂዎች በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው የቀሰሙትን ዕውቀት፣ ክህሎትና የምርምር ውጤቶች ወደ ተግባር በመቀየር የሀገሪቱን ሁለንተናዊ ዕድገትና የሕዝቡን ሕይወት ለማሻሻል የበኩላቸውን አዎንታዊ ሚና እንዲጫወቱ ጥሪ አቅርበዋል። ምሩቃኑ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲን መልካም ስም የሚያስጠሩ ብቁ አምባሳደሮች እንደሚሆኑ ሙሉ እምነታቸውን የገለጹት ፕሬዝደንቱ፣ ለተመራቂዎቹ መልካም የሥራ ዘመንም ተመኝተዋል።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት / / አብደላ ከማል ባደረጉት ንግግር ተቋሙ የመማር-ማስተማር፣ የምርምርና የማኅበረሰብ አገልግሎት ሥራዎችን ይበልጥ ለማሳለጥና ጥራቱን ለማሻሻል በቁርጠኝነት እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል። ፕሬዝደንቱ ለተመራቂዎች ባስተላለፉት መልእክት፥ ዛሬ የተቀበሉት ዲግሪ የዓመታት ጥረታቸው ማረጋገጫና የታላቅ ስኬት መጀመሪያ እንጂ የትምህርት ጉዟቸው ማክተሚያ እንዳልሆነ አሳስበው፣ የአሁኑ ዓለም በከፍተኛ ፍጥነት እየተለወጠ በመሆኑ ተመራቂዎች ያገኙትን ዕውቀት ብቻ ይዘው ሳይቀመጡ ራሳቸውን ዘወትር ማሻሻልና ማዘመን እንዳለባቸው አጽንኦት ሰጥተዋል።

በምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የሳውላ ካምፓስ ኃላፊ አቶ ዘለቀ ዶሳ ካምፓሱ 2008 . ሥራ ሲጀምር 4 የትምህርት ፕሮግራሞች ብቻ የነበረ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት የትምህርት ጥራትንና ተደራሽነትን በማስፋት የፕሮግራሞቹን ቁጥር ወደ 29 ማሳደግ መቻሉን ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅትም ካምፓሱ 2 ሺህ 500 በላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ በማስተማር ላይ እንደሚገኝ አብራርተዋል። ካምፓሱ በሁሉም ዘርፎች  ዕድገት እያስመዘገበ መሆኑን የጠቀሱት አቶ ዘለቀ፣ በተለይም ዩኒቨርሲቲው ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ዘመናዊ የላቦራቶሪ መሠረተ-ልማት መገንባቱንና ተማሪዎችም ለምርምርና ለተግባራዊ ትምህርት ሥራዎች በስፋት እየተጠቀሙበት እንደሚገኝ አስታውቀዋል።

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ምሩቃን (አሉምናይ) ማኅበር ፕሬዝዳንት አቶ ኤርሚያስ ዓለሙ ባስተላለፉት መልእክት የአሁኑ ዓለም የሚፈልገው የወረቀት ዲግሪን ብቻ ሳይሆን ችግር ፈቺ ሰዎችን ጭምር መሆኑን በመጠቆም፣ ተመራቂዎች ማኅበረሰባዊ ችግሮችን ወደ መልካም ዕድል (opportunities) የሚቀይሩ መሆን እንዳለባቸው መክረዋል። የዕለቱ ምሩቃን ከዛሬ ጀምሮ የዩኒቨርሲቲው አምባሳደሮች መሆናቸውን የጠቀሱት አቶ ኤርሚያስ በተሰማሩበት የሥራ መስክ ሁሉ በቅንነትና በታማኝነት ሀገራቸውንና ሕዝባቸውን እንዲያገለግሉ እንዲሁም የተቋሙን መልካም ስም እንዲያስጠሩ ጥሪ አቅርበዋል። በመጨረሻም ምሩቃኑ ከእናት ተቋማቸው ጋር ያላቸውን ትስስር ይበልጥ እንዲያጠናክሩና የዩኒቨርሲቲውን የቀድሞ ምሩቃን ማኅበርን እንዲቀላቀሉ አሳስበዋል።

በሥነ-ሥርዓቱ ማጠቃለያ ላይም የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የማበረታቻ ሽልማቶች ተበርክተዋል። በዚህም መሠረት ከየኮሌጆቹ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ሴት ምሩቃን ልዩ ሽልማት የተሰጠ ሲሆን፣ በየዘርፋቸው በከፍተኛና የላቀ ውጤት አንደኛ ለወጡ ተማሪዎች ደግሞ የወርቅ ሜዳሊያ ተበርክቶላቸዋል።

 ካምፓሱ 8 ዓመታት ጉዞው የዛሬዎቹን ጨምሮ 2540 ምሩቃንን ለሀገር አበርክቷል።

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ

የጥበብ ምንጭ!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት