በየዓመቱ በኢትዮጰያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አዘጋጅነት የሚካሄደው የታዳጊ ወጣቶች እግር ኳስ ውድድር ዘንድሮ ለ3 ጊዜ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ከሐምሌ 10/2016 ጀምሮ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ስፖርት አካዳሚ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አሰግድ ከተማ እንደገለጹት በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲና አከባቢው በእግር ኳስ ዘርፍ ከፍተኛ አቅምና ፍላጎት ያላቸው ወጣቶች ያሉበት በመሆኑ ዩኒቨርሲቲው ፍላጎት ያላቸውን ታዳጊ ወጣቶች በፕሮጀክት አደራጅቶ እያሠለጠነ ይገኛል፡፡ ዳይሬክተሩ በታዳጊ ወጣቶች እግር ኳስ ውድድር በመጀመሪያ ዓመት ተሳትፎ በሴቶች ዋንጫ ማንሳታቸውንና በሁለተኛ ዓመት ወንዶች እግር ኳስ ቡድንም 3 ደረጃ በማግኘት ማጠናቀቃቸውን ያስታወሱ ሲሆን ዘንድሮም በሁለቱም ፆታዎች በ8ቱ ቡድኖች ውስጥ ማለፋቸውን ተናግረዋል፡፡ በውድድሩ በአጠቃላይ አምስት ዩኒቨርሲቲዎችን፣ ዞኖችንና ከተማ አስተዳደሮችን ጨምሮ በሁለቱም ፆታዎች 28 ቡድኖች እየተሳተፉ እንደሚገኝ አቶ አሰግድ ጠቁመዋል፡፡

አቶ አሰግድ የውድድሩ ዓለማ በአካባቢው የእግር ኳስ ችሎታ ላላቸው ታዳጊ ወጣቶች የሥራ ዕድል መፍጠርና ተተኪ የእግር ኳስ ተጫዎቾችን ማፍራት መሆኑን አክለው ከዚሁ ጋር በተያያዘም በፕሮጀክቱ ሲሳተፉ የነበሩ 16 ወጣቶች በአሁኑ ሰዓት በሀገሪቱ በተለያዩ ክለቦች ውስጥ እየተጫወቱ እንደሚገኙ ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ

የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCAD/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት