ሐምሌ 3 ቀን 2017 ዓ.ም
የክረምት ተማሪዎች የመግቢያ ጥሪ ማስታወቂያ
ለአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ነባር የክረምት ተማሪዎች በሙለ፤
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ቅድመ-ምረቃ እና ድህረ-ምረቃ ፕሮግራም በክረምት መርሃ ግብር ትምህርታችሁን ስትከታተለ ሇነበራችሁ ነባር ተማሪዎች የ2017 ዓ.ም ትምህርት ዘመን የመግቢያ ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ሐምሌ 12 እና 13 ቀን 2017 ዓ.ም እንድሁም የምዝገባ ቀን ሰኞ እና ማክሰኞ ሐምሌ 14 እና 15 ቀን 2017 ዓ.ም በየካምፓስ፣ በየኮሌጅ፣ በየኢንስቲቲዩት ሬጅስትራር ማስተባበሪያ ጽ/ቤቶች የሚካሄድ ሲሆን ትምህርት የሚጀመረው ከምዝገባው ጎን ሇጎን ሰኞ ሐምሌ 14 ቀን 2017 ዓ.ም እንዲሆን ተወስኗል፡፡ በመሆኑም በተጠቀሱት ቀናትና ቦታዎች በመገኘት ምዝገባ መፈጸም እና ትምህርት መጀመር የምትችለ መሆኑን በጥብቅ እናሳውቃሇን፡፡
ማሳሰቢያ፡- ከላይ ከተጠቀሱት ቀናት ቀድመውም ይሁን ዘግይተው የሚመጡ ተማሪዎችን ዩኒቨርሲቲው የማያስተናግድ መሆኑን ያሳውቃል፡፡
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሬጂስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ