የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሥነ-ምግባር እና ፀረ-ሙስና መከታተያ ዳይሬክቶሬት ተመራቂ ተማሪዎች ተመርቀው በሚሄዱበት የተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚገጥሟቸውን አዲስ የሥራ አካባቢዎችና የሚሰጣቸውን ኃላፊነት በጥንቃቄ በመቀበል የሚሰጧቸውን ማኅበራዊ አገልግሎቶች ሥነ ምግባራዊ እንዲያደርጉ በሥራ ሥነ ምግባር መርሆዎች እና በሙስና ወንጀል ሕጎች ዙሪያ ግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና አዘጋጅቷል፡፡ ስለሆነም ተመራቂ ተማሪዎች በሙሉ ከዚህ በታች በተያዘላችሁ ፕሮግራም መሠረት ሥልጠናውን እንድትካፈሉ እናሳስባለን፡፡


 ዓርብ ቀን 21/10/2016 ዓ.ም ጧት ከ2፡00 - 6፡00 በኩልፎ ካምፓስ LT-1
    አዳራሽ
 ቅዳሜ ቀን 22/10/2016 ዓ.ም ከሰዓት ከ8፡00 - 11፡00 ጫሞ ካምፓስ
    በተማሪዎች ካፌ
 ሰኞ ቀን 24/10/2016 ዓ.ም ጧት ከ2፡00 - 6፡00 በዋናው ግቢ ቴክኖሎጂ አዳራሽ
     እንዲሁም ከሰዓት ከ8፡00 - 11፡00 ሰዓት በአባያ ካምፓስ አዲሱ የማኔጅመንት ሕንጻ አዳራሽ
 ማክሰኞ ቀን 25/10/2016 ዓ.ም ከ8፡00 - 11፡00 በሳውላ ካምፓስ ተማሪዎች ካፌ
     በመገኘት ሥልጠናውን እንድትካፈሉ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

ማሳሰቢያ፡- በሥልጠናው በንቃት ለሚሳተፉ ተመራቂ ተማሪዎች ሰርተፍኬት የሚዘጋጅ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCAD/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት