የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ላለፉት ሁለት አሥርት ዓመታት ገደማ በሕክምና ትምህርት፣ በምርምርና በሕክምና አገልግሎት ዘርፍ አብሮት ለሰራውና የላቀ አስተዋፅኦ ላበረከተው ለአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል ታሪካዊ የምስጋና እና የእውቅና መርሃ ግብር ነሐሴ 7/2018 . አካሂዷል። ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

በዕለቱ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት / ኢንጂነር አብደላ ከማል ባስተላለፉት ዋና መልዕክት፣ አርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል ለዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ዋነኛ የመማሪያ፣ የምርምር እና የተግባር ልምምድ (Attachment Site) ሆኖ በመቆየት ብቁ ሐኪሞችንና የጤና ባለሙያዎችን ለማፈራት ላደረገው በዋጋ የማይተመን አስተዋፅኦ ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል። ፕሬዝዳንቱ አፅንዖት ሰጥተው እንደተናገሩት፣ በአሁኑ ወቅት የተደረገው የባለሙያዎች ሽግግር የሁለቱን ተቋማት ግንኙነት የሚያቆም ሳይሆን፣ በዩኒቨርሲቲው እና በአጠቃላይ ሆስፒታሉ እንዲሁም በአካባቢው በሚገኙ የጤና ተቋማት መካከል ያለው አጋርነትና ትብብር በቀጣይም በተሻለ ጥራትና አቅም ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል።

 

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያና ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ቦርድ ሰብሳቢና የምርምርና ትብብር ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ተክሉ ወጋየሁ ባስተላለፉት መልዕክት፣ አርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል ለዩኒቨርሲቲው የጤናና ሕክምና ትምህርት የተግባር ልምምድ ማዕከል በመሆን ላበረከተው አስተዋፅኦ ምስጋና አቅርበዋል። የተደረገው የባለሙያዎች ሽግግር የሕብረተሰቡን አገልግሎት ሳይጎዳ መከናወኑ አርአያነት ያለው መሆኑን ገልጸው፣ በቀጣይም በጋራ ሥራዎች ላይ ትብብሩ እንደሚቀጥልና ለዚህም የዩኒቨርሲቲው ቦርድ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።

 

የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር / ደስታ ጋልቻ በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር የሁለቱን ተቋማት ታሪካዊ የትብብር ጉዞና የደረሱበትን የዕድገት ምዕራፍ በሰፊው አብራርተዋል። / ደስታ እንዳመለከቱት፣ እስከ 2003 . ድረስ ተቋም ለተቋም ምንም ዓይነት የጽሁፍ ውል ሳይኖር የሆስፒታሉ ባለሙያዎችን እንደ እንግዳ መምህርነት ሲጠቀም የቆየ ቢሆንም፣ በኋላ ላይ የልምድ ልውውጥ በማድረግ በተዘጋጀ የጋራ መግባቢያ ስምምነት (MOU) መሠረት የተቀናጀና ስልታዊ ሥራ ሲከናወን ቆይቷል። ዩኒቨርሲቲውም ከአገልግሎት ማግኘት ባሻገር ለሆስፒታሉ እንደ አልትራሳውንድ፣ አልጋዎች፣ ኮምፒውተሮች፣ ፕሪንተሮች እና ልዩ ልዩ የቢሮ ቁሳቁሶችን በድጋፍ ሲያቀርብ መቆየቱን አወስተዋል።

 

/ ደስታ አክለውም የማስተማሪያና ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታሉ ከታህሳስ 16/2018 . ጀምሮ ተኝቶ ሕክምናን ጨምሮ ሰፊ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ተከትሎ፣ የሥራ መስተጓጎል እንዳይፈጠር በተዋቀረው "Exit Strategy" ኮሚቴ ምክረ-ሐሳብ መሠረት ውጤታማ የሥራ ሽግግር መደረጉን ገልጸዋል። በዚህም መሠረት በልዩ ሁኔታ ስምምነት ከተደረገባቸው አገልግሎቶች (እንደ ፊስቱላ እና ፕላስቲክ ሰርጀሪ ያሉ) በስተቀር ከነሐሴ 1/2018 . ጀምሮ የዩኒቨርሲቲው ባለሙያዎች ሙሉ በሙሉ ወደ ዩኒቨርሲቲው ሆስፒታል መጠቃለላቸውን አስረድተዋል።

 

በመርሃ ግብሩ ላይ የአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተርና የሆስፒታሉ ሥራ አስኪያጅ ተወካይ / አዲሱ ተስፋዬ በበኩላቸው ለተደረገው ታሪካዊ የእውቅናና የምስጋና ፕሮግራም የላቀ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። / አዲሱ ሁለቱ ተቋማት ባለፉት ሁለት አሥርት ዓመታት ገደማ ውስጥ እጅግ ውጤታማና ፍሬያማ የጋራ ሥራዎችን ማከናወናቸውን ገልጸዋል። አክለውም የተደረገው የሥራና የባለሙያዎች ሽግግር የማህበረሰቡን የሕክምና አገልግሎት በማይጎዳና በማያስተጎጉል መልኩ መጠናቀቁን ገልጸው፣ ዩኒቨርሲቲው እስካሁን ላደረገው በዋጋ የማይተመን ድጋፍ አመስግነው ይህ ታዊ አጋርነት በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና እንደማይቋረጥ አረጋግጠዋል።

 

በታሪካዊው የእውቅና መርሃ ግብር ላይ የቦርድ ሰብሳቢና የምርምርና ትብብር ምክትል ፕሬዝደንት / ተክሉ ወጋየሁ፣ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት / ቦጋለ ገብረማሪያም፣ አስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ጳውሎስ ታደሰ እንዲሁም የሁለቱ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮችና ባለሙያዎች ተገኝተዋል።

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ

የጥበብ ምንጭ!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት