አቶ አሸናፊ ፊሊጲዮስ ከአባታቸው ከአቶ ፊሊጲዮስ ኮቦቶ እና ከእናታቸው ከወ/ሮ አባይነሽ ባባንቶ በጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ከተማ ኅዳር 1/1979 ዓ/ም ተወለዱ፡፡

የመጀመርያ ደረጃ ትምህርታቸውን በአርባ ምንጭ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እንዲሁም የ2ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአርባ ምንጭ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃና መሰናዶ ት/ቤት የተከታተሉ ሲሆን በአርባ ምንጭ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በአውቶሞቲቭ ኢንጂን ሰርቪሲንግና ሜካኒክስ በደረጃ III ከታኅሣሥ 20/2003 - ታኅሣሥ 1/ 2005 ዓ/ም ሠልጥነዋል፡፡

አቶ አሸናፊ ከኅዳር 1/2008 ጀምሮ ሕይወታቸው እስካለፈበት ጊዜ ድረስ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የሥራ ክፍሎች ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡

አቶ አሸናፊ ፊሊጲዮስ ባደረባቸው ድንገተኛ ሕምም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው በ38 ዓመታቸው ኅዳር 23/2017 ዓ/ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡ አቶ አሸናፊ የአንድ ሴት እና የሦስት ወንድ ልጆች አባት ነበሩ፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በአቶ አሸናፊ ፊሊጲዮስ ኅልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን እየገለጸ ለሟች ቤተሰቦች፣ ወዳጅ ዘመዶች፣ ጓደኞችና የሥራ ባልደረቦች እንዲሁም ለዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ መጽናናትን ይመኛል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት