በአርባ ምንጭ ውኃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በ‹‹Water Resources & Irrigation Engineering›› ፋከልቲ በ ‹‹Ground Water Engineering›› ትምህርት ፕሮግራም የ3ኛ ዲግሪ ትምህርቱን ሲከታተል የቆየው ዕጩ ዶ/ር አስናቀው ሙሉዓለም   የመመረቂያ ጽሑፍ ጥቅምት 18/2017 ዓ.ም የውጭና የውስጥ ገምጋሚዎች እንዲሁም አማካሪዎች በተገኙበት ቀርቦ ተገምግሟል፡፡ የመመረቂያ ጹሑፉ አስፈላጊውን መስፈርት በማሟላቱ በአማካሪ ቦርዱ ተቀባይነት አግኝቶ ጸድቋል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

ዕጩ ዶ/ር አስናቀው ሙሉዓለም የመጀመሪያ ዲግሪውን ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በ‹‹ Water & Resource Engineering››   እንዲሁም 2ኛ ዲግሪውን ከጂማ ዩኒቨርሲቲ በ ‹‹Hydraulic Engineering›› ያገኘ ሲሆን የ3ኛ ዲግሪ ትምህርቱን በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሲከታተል ቆይቶ የመመረቂያ ጹሑፉን ‹‹Evaluation of Groundwater Potential and Quality in The Guna-Abay Watershed: Upper Abay (Blue Nile) Basin, Ethiopia›› በሚል ርእስ አከናውኗል፡፡

የዕጩ ዶ/ር  አስናቀው ሙሉዓለም ውጤት ለዩኒቨርሲቲው ሴኔት ቀርቦ ተቀባይነት ሲያገኝ የሚመረቅ ይሆናል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ

የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCAD/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት