በአርባ ምንጭ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ማኅበረሰብ ጉድኝት ዳይሬክቶሬት የቀረቡ 5 ንድፈ ሃሳቦች የኢንስቲትዩቱ  ተመራማሪዎችና መምህራን በተገኙበት ኅዳር 19/2015 ዓ.ም ተገምግመዋል፡፡ ምስሎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

የኢንስቲትዩቱ ም/ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር ደመላሽ ወንድማገኘሁ እንደገለጹት የቀረቡ የጥናት ውጤቶች መሬት ላይ የሚታዩ የማኅበረሰቡን ችግሮች በግልጽ የሚያሳዩ ናቸው፡፡ ዶ/ር ደመላሽ የቀረቡት የተገመገሙት ንድፈ ሃሳቦች ጸድቀው ተግባራዊ እስከሚደረጉ ድረስ ኢንስቲትዩቱ በትኩረት ክትትልና ድጋፍ እንደሚያደርግ ጠቁመዋል፡፡

የኢንስቲትዩቱ የማኅበረሰብ ጉድኝት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር መ/ርት ፌቨን ክንፈ ኢንስቲትዩቱ የማኅበረሰብ ጉድኝት ዳይሬክቶሬት በ2014 ዓ.ም ባወጣው ማስታወቂያ ጥሪ መሠረት ከኢንስቲትዩቱና  ከ4ቱ ፋከልቲዎች  በዘርፉ ሊያሠሩ የሚችሉ በጥናት የተረጋገጡ 5 ንድፈ ሃሳቦች ቀርበው ተገምግመዋል ብለዋል፡፡ የንድፈ ሃሳቦቹም ይዘት  በአብዛኛው የውሃ አማራጮችን ማጥናት፣ የከርሠ-ምድር ውሃ በማጥናትና በመለየት የማኅበረሰቡን የንጹህ መጠጥ ውሃ ችግር መቅረፍ እንዲሁም የኩልፎን ወንዝ ውሃ ለመስኖ በመጠቀም የጋሞ እርሻ ልማት፣ ቆላ ሻራ፣  ጫኖና ላንቴ አካባቢዎችን የመስኖ ተጠቃሚ ማድረግ የሚሉት ይጠቀሳሉ ብለዋል፡፡

የኢንስቲትዩቱ ውሃ ሀብትና መስኖ ምኅንድስና መ/ር የሆኑት መ/ር መሐመድ ሁሴንና መ/ር ሰልማን ሀሰን የተባሉት በጋራ ካቀረቡት ሁለት ንድፈ ሃሳቦች መካከል አንዱ “Improving the Drainage Performance of Storm drainage System of Woze Keble, Arba Minch”  በሚል ርዕስ የቀረበ ሲሆን ይህም በአርባ ምንጭ ከተማ በወዜ ቀበሌ የፍሳሽ ውሃ መውረጃ ችግር ምክንያት በሰውና በንብረት ላይ የሚደርሰውን ጉዳት በዘላቂነት ለመፍታት ታስቦ የቀረበ ንድፈ ሃሳብ ነው ብለዋል፡፡

ለግምገማ ከቀረቡ ንድፈ ሃሳቦች መካከል “Identifying Groundwater Reserves and Enabling Food Security in Rural Communities: Case Study of Kogota Woreda, Gamo Zone, Ethiopia”፣ “Development of Irrigation Infrastructure and Demonstration of Modern Irrigation System at Arba Minch, Ethiopia”፣ “Improving the Drainage Performance of Storm Drainage System of Woze Kebele, Arba Minch” እና “Adoption of Irrigation Water Management Practices in Dere Malo Woreda, Gamo Zone, Ethiopia” ተጠቃሽ ናቸው፡፡

የኢንስቲትዩቱ ውሃ አቅርቦትና አካባቢ ምኅንዲስና ፋከልቲ መምህርና ተመራማር ዶ/ር አቡኑ አጥላባቸው ስለቀረቡት ንድፈ ሃሳቦች አስተያየት ስሰጡ እንደተናገሩት ንድፈ ሃሳቦቹ በአብዘኛው አግባቢነት ያላቸውና የኅብረተሰቡን ችግር በትክክል የለዩ ናቸው ብለዋል፡፡

በፕሮግራሙ የአርባ ምንጭ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ም/ሳይንቲፍክ ዳይሬክተር ዶ/ር ደመላሽ ወንድማገኘሁና የኢንስቲትዩቱ የማኅበረሰብ ጉድኝት ዳይሬክተር መ/ርት ፌቨን ክንፈን ጨምሮ የኢንስቲትዩቱ መምህራንና ተመራማሪዎች ተሳትፈዋል፡፡  

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት