አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የማጠቃለያ ፈተና ተፈትነው የማካካሻ ትምህርት/Remedial Program/ ፕሮግራም ለመከታተል ያለፉትን ተማሪዎች በትምህርት ሚኒስቴር በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት በግል ከፍሎ ለመማር የሚፈልጉ የተፈጥሮ ሳይንስ እና የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል፡፡
- የመመዝገቢያ መስፈርቶች
በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የማጠቃለያ ፈተና ተፈትነው የማካካሻ ትምህርት/Remedial/ ፕሮግራም ለመከታተል ያለፉ (እንደተፈተኑት የትምህርት ዓይነት ብዛት 30% ከመቶ እና ከዚያ በላይ ማለትም (210 ከ 700፣ 180 ከ 600 እና 150 ከ 500) የተቆረጠውን ነጥብ የሚያሟሉ፡፡
- የሚያስፈልጉ የትምህርት መረጃዎች
- E.S.L.C.E/EHEEQC የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመግቢያ ውጤት ካርድ ኦርጅናልና የማይመለስ ሁለት ፎቶ ኮፒ
- ከ9ኛ - 12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ኦርጅናልና የማይመለስ ሁለት ፎቶ ኮፒ
- የማይመለስ ሁለት ዶሴ (ክላሰር) እና ሁለት ጉርድ ፎቶ ግራፍ
- የማመልከቻ ክፍያ ብር 00 /ሀምሳ ብር/ ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000021480502 ገቢ የተደረገበትን ደረሰኝ ከማስረጃቸዉ ጋር ማያያዝ::
- የ8ኛ ክፍል ሚኒስትሪ ካርድ ኦርጅናልና የማይመለስ ሁለት ፎቶ ኮፒ
- የማመልካቻ ቦታ
ሀ) አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ነጭ ሣር ካምፓስ የተከታታይና ርቀት ትም/ት ኮሌጅ ሬጅስትራር ጽ/ቤት
ለ)አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሳውላ ካምፓስ የተከታታይ ትም/ት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት(የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ብቻ)
- የምዝገባ ጊዜ - ከየካቲት 27/2015 - መጋቢት 07/2015 ዓ.ም ድረስ
ለተጨማሪ መረጃ - በ046-181-5468 እና 046-181-0228 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
ጥራት ያለው ትምህርት መለያችን ነው!!
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተከታታይና ርቀት ትምህርት ኮሌጅ