ወ/ሮ የኔነሽ ደሱ ከአባታቸው አቶ ደሱ ሀጎስ እና ከእናታቸው ከወ/ሮ ንጋቷ ገብሬ ጥር 21/1975 ዓ.ም በአርባ ምንጭ አባያ ክፍለ ከተማ ተወለዱ፡፡
ወ/ሮ የኔነሽ ደሱ ከሰኔ 1/2005 ዓ/ም ጀምሮ የተማሪዎች ምግብ አገልግሎት ዝግጅት የወጥ ቤት ሠራተኛ በመሆን ሕይወታቸው እስካለፈበት ቀን ድረስ ዩኒቨርሲቲውን ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡
ወ/ሮ የኔነሽ የሦስት ልጆች እናት ሲሆኑ ባደረባቸው ሕመም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው መስከረም 20/2017 ዓ/ም በ42 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በወ/ሮ የኔነሽ ደሱ ሞት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለሥራ ባልደረቦቻቸውና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን ይመኛል፡፡
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-
ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCAD/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA
የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት