የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሙያ ማበልጸጊያ ማዕክል ከደረጃ ዶት ኮም/Dereja.com/ እና ከማስተር ካርድ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር ከጋሞ ዞን የተለያዩ ወረዳዎችና ከአርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደር በ2015/16 ዓ.ም በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቀው በዞኑ ሥራ ዕድል ፈጠራና ልማት ኢንተርፕራይዝ ቢሮ ለተመዘገቡ ከ270 በላይ ሥራ ፈላጊ ወጣቶች ከነሐሴ 3/2016 ዓ.ም ጀምሮ ለሦስት ወራት የሚቆይ የ"Deraja Academy Accelerator Program (DAAP)" ሰዋዊና ሙያዊ ክሂሎት ሥልጠና እየሰጠ ነው፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
በሥልጠናው የመጀመሪያ ክፍል ሰዋዊ ክሂሎት(Soft Skill) የሚባሉትን ‹‹Self Discover››፣ ‹‹Building Self-image››፣ ‹‹Communication Skill›› የሚሉትን ጨምሮ በስምንት ሞጁሎች ለስምንት ሳምንታት የሚሠለጥኑ ሲሆን በሁለተኛው ክፍል ሙያዊ ክሂሎት(Professional Skill) ከሚባሉት ‹‹Customer Service››፣ ‹‹Sales and Marketing››፣ ‹‹Finance and Accounting›› የሚሉትን ጨምሮ ከሰባት ሞጁሎች አንዱን በመምረጥ በዘርፉ ከፍተኛ ልምድ ባለቸው ባለሙያዎች ለአንድ ወር በኦንላይን/Online/ በመሠልጠን ሲያጠናቅቁ የምስክር ወረቀት የሚያገኙ ይሆናል፡፡
ሥልጣናው ተማሪዎች ተቀጥረውም ሆነ የራሳቸውን ሥራ ፈጥረው እንዲሠሩ እንዲሁም ተጨማሪ የትምህርት ዕድል እንዲያገኙ የሚረዳቸው ሲሆን ‹‹Dereja.com›› በሚያዘጋጀው የሥራ ዐውደ ርእይና አፍሪካ ጆብስና በሌሎች መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት በሚያወጧቸው የሥራ ማስታወቂያዎች ልምድ ካላቸው ባለሙያዎች እኩል ተወዳድረው መቀጠር እንዲችሉ የሚያደርግ ነው፡፡
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-
ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCAD/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA
የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት