አቶ ደሳለኝ አባይነህ ከአባታቸው ከአቶ አባይነህ አግሮ እና ከእናታቸው ከወ/ሮ አስናቀች ዳርሳ በወላይታ ዞን ሁምቦ ወረዳ መጋቢት 10/1978 ዓ/ም ተወለዱ፡፡

የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በወላይታ ዞን ሁምቦ ወረዳ ጉታቶ ላሬና ሙሉ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተከታትለዋል፡፡

አቶ ደሳለኝ ከሰኔ 1/2005 ዓ/ም ጀምሮ ሕይወታቸው እስካለፈበት ጊዜ ድረስ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች አገልግሎት ዳይሬክቶሬት የምግብ አስተናጋጅና የጽዳት ሠራተኛ ሆነው ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡

አቶ ደሳለኝ ባደረባቸው ሕመም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው መስከረም 06/2017 ዓ/ም በ39 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡ አቶ ደሳለኝ ባለትዳርና የሁለት ልጆች አባት ነበሩ፡፡

ዩኒቨርሲቲው በአቶ ደሳለኝ አባይነህ ኅልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን እየገለጸ ለሟች ቤተሰቦች፣ ወዳጅ ዘመዶች፣ ጓደኞችና የሥራ ባልደረቦች እንዲሁም ለዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ መጽናናትን ይመኛል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ

የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCAD/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት