የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የብዝኃ ሕይወት ምርምርና ጥበቃ ማዕከል የስፔን ዝርያ ዱባ ላይ ባካሄደው የሙከራ ምርምር የተሻለ ምርት ማግኘት መቻሉን ገልጿል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የምርምር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ተስፋዬ ሀ/ማሪያም እንደገለጹት በምርምር ጣቢያው ለተመራማሪዎች በሚሰጣቸው መሬት ላይ የተለያዩ የምርምር ሥራዎች መካከል ከሌላ አካባቢ የሚመጡ ዝርያዎችን የመሞከር ሥራ ነው፡፡ ከዚህም አንዱ የስፔን ዝርያ የሆነው ዱባ ሲሆን ለሙከራ በተደረገው ምርምር አመርቂ ውጤት የታየበት መሆኑን ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው የብዝኃ ሕይወት ምርምር ማዕከል ተመራማሪ አታላይ አዘነ በበኩላቸው ማዕከሉ የተለያዩ የዕፅዋት ዝርያዎችን በመሰብሰብ፣ በማቆየት፣ በመመራመርና በማላመድ እንዲሁም የተሻለውን የምርት ዝርያ ለአርሶ አደሩና ለማኅበረሰቡ ለማሰራጨት እንደሚሠራ ገልጸዋል፡፡ በማዕከሉ የተሞከረው የስፔን ዝርያ ዱባ በ20 እና በ40 ሳ.ሜትር ርቀት ዱባ የሚጥል በመሆኑ ምርታማነቱ የበለጠና ተመራጭ እንደሚያደርገው ተመራማሪው ተናግረው መሰል ዝርያዎችን በማላመድ ለአርሶ አደሩ በማሰራጨት አርሶ አደሩን ተጠቃሚ ለማድረግ ይሰራል ብለዋል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCCD/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት