ዶ/ር ኢንጂነር ቦጋለ ገብረማርያም በ1981 የመጀመሪያ ዲግሪ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ ‹‹Civil Engineering››፣ በ1986 ዓ/ም ድኅረ ምረቃ ዲፕሎማ (Post Graduate Diploma) በ‹‹Hydraulic Engineering (Hydro informatics)›› ኔዘርላድ ሀገር ከሚገኘው ‹‹International Institute for Infrastructural, Hydraulic and Environmental engineering (IHE), Delft››፣ በ1987 ዓ/ም ከዚሁ ተቋም በ‹‹Hydraulic Engineering (Hydro informatics)›› የማስተርስ ዲግሪ፣ በ2000 ዓ/ም ጀርመን ከሚገኝ ‹‹Freie University of Berlin›› በ‹‹Lake Hydrodynamics›› የትምህርት ዘርፍ የሦስተኛ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል፡፡
ከ1982-1988 ዓ/ም በሐሮማያ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የአካዳሚክ ደረጃዎች በመምህርነት ያገለገሉት ዶ/ር ኢ/ር ቦጋለ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከ1988 ዓ/ም ጀምሮ በነበራቸው የረዥም ጊዜ አገልግሎት በርካታ የመጀመሪያ፣ የሁለተኛና ሦስተኛ ዲግሪ ኮርሶችን በመስጠትና ተማሪዎችን በማማከር ማስመረቅ ችለዋል፡፡ በዚህም የአራት የ3ኛ ዲግሪና 130 በላይ የ2ኛ ዲግሪ ተማሪዎች ምርምር አማካሪ በመሆን እንዲሁም የውጭ ፈታኝ በመሆን ሠርተዋል፡፡
ዶ/ር ኢ/ር ቦጋለ ከማስተማር ሥራቸው በተጨማሪ በተለያዩ የኃላፊነት ደረጃዎች ዩኒቨርሲቲውን ያገለገሉ ሲሆን የሃይድሮሊክ ትምህርት ክፍል ኃላፊ ተወካይ፣ ከ1990 ዓ/ም- 1994 ዓ/ም የውኃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት አካዳሚክና ምርምር ም/ዲን፣ ከጥቅምት 1994-ሰኔ 1994 የቀድሞው የአርባ ምንጭ ውኃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ተ/ዲንና የአካዳሚክና ምርምር ም/ዲን፣ ከ1999- 2000 ዓ/ም የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክና ምርምር ም/ፕሬዝደንት እንዲሁም ከየካቲት 2015 ዓ/ም እስከ ኅዳር 2017 ዓ/ም የአርባ ምንጭ ውኃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ሆነው ሠርተዋል፡፡
በዩኒቨርሲቲው የሃይድሮሊክ ምኅንድስና ተባባሪ ፕሮፌሰር የሆኑት ዶ/ር ኢ/ር ቦጋለ በተለያዩ የመስኖና ግድብ ፕሮጀክቶች ውስጥ በመሳተፍ ሙያቸውን በተግባር ያዋሉ ሲሆን ለአብነት ያህል ‹‹Feasibility Study and Detail Design of Chalko Dam and Irrigation Development››፣ ‹‹Study and Design of Abattoir Service››፣ ‹‹Study of Solid Waste Management System and Landfill Design›› የተሰኙ ፕሮጀክቶች የፕሮጀክት ማኔጀር በመሆን ሰርተዋል፤ እየሰሩም ይገኛሉ፡፡ በምርምሩ ዘርፍም ከፍተኛ ሚና ያለቸው ዶ/ር ኢ/ር ቦጋለ 20 የሚሆኑ የምርምር ሥራዎቻቸውን በታወቁ የምርምር ጆርናሎች ላይ ማሳተም ችለዋል፡፡
ዶ/ር ኢ/ር ቦጋለ በእስከ አሁን ቆይታቸው በመማር ማስተማር፣ በምርምር እንዲሁም በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ዩኒቨርሲቲውን በትጋት ሲያገለግሉ መቆየታቻውን ታሳቢ በማድረግ የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ቦርድ ከታኅሣሥ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝደንት ሆነው በውክልና እንዲያገለግሉ መድቧቸዋል፡፡
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለዶ/ር ኢ/ር ቦጋለ ገብረማርያም መልካም የሥራ ዘመን እንዲሆንላቸው መልካም ምኞቱን ይገልጻል፡፡
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-
ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA
የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት