የፌዴራል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ከትምህርት ሚኒስቴርና ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ከወልቂጤ፣ ወራቤ፣ ዋቸሞ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ጂንካ  እና አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲዎች ለመጡ የግዥና ንብረት እንዲሁም የፋይናንስና በጀት አስተዳደር ኃላፊዎች፣ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች፣ የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና መከታተያ ክፍል ሥራ አስፈጻሚዎች፣ የተማሪዎች አገልግሎት ኃላፊዎች፣ የግንባታ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ኃላፊዎችና ሌሎች የሚመለከተቸው አካላት ሙስናን መከላከልና መቆጣጠርን አስመልክቶ ከታኅሣሥ 05 - 06/2016 ዓ/ም የሚቆይ የመጀመሪያ ዙር ሥልጠና በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ እየሰጠ ይገኛል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

የሥልጠናው ዓላማ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ በግዥ ላይ የሚፈጸመውን ሙስና የመከላከል አቅምን በማሳደግ ከሙስናና ብልሹ አሠራር የጸዳ የግዥ ሥርዓት እንዲከተሉ ማስቻል ነው፡፡

በሥልጠናው ‹‹በመንግሥት ግዥ ላይ የሚፈጸም ሙስናን መከላከል›› እና ‹‹ሥነ ምግባራዊ አመራር›› የሚሉ ሠነዶችን ጨምሮ አራት የሥልጠና ሠነዶች የሚቀርቡ ይሆናል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ

የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCCD/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት