አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በቅርቡ የመሬት መንሸራተት አደጋ በተከሰተበት ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ የደረሰውን የመሬት መንሸራተት አደጋ አስመልክቶ ከተለያየ ዘርፍ የተወጣጡ ተመራማሪዎችን ወደ ቦታው በመላክ የአደጋውን መንስኤና ቀጣይ የአደጋ ስጋቶች እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ሥነ ልቦናዊ ጉዳቶችን ለማወቅ ያካሄደው ፈጣን የዳሰሳ ጥናት ያለበት ደረጃ ነሐሴ 06/2016 ዓ/ም የዩኒቨርሲቲው አመራሮችና ተመራማሪዎች በተገኙበት ቀርቦ ተገምግሟል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
የጥናት ቡድኑ በዕለቱ የተሰጡ አስተያየቶችንና መካተት ያለባቸውን ጉዳዮች እንዲሁም ቀሪ የመስክ ላይ መረጃዎችን በማጠናቀቅ የአደጋውን መንስኤ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ሥነ ልቦናዊ ጉዳቶችን፣ መሰል አደጋ ሊከሰት የሚችልባቸው ቦታዎችን የሚያመላክት ካርታ የማዘጋጀት፣ አካባቢው ከዚህ በኋላ ለመሰል አደጋዎች ያለው ተጋላጭነትና የነዋሪዎቹን ቀጣይ ዕጣ ፋንታ አስመልክቶ በሳይንሳዊ መረጃዎች ላይ የተመሠረተ ዝርዝር የግኝት ውጤት ገለጻና ምክረ ሃሳብ በቅርቡ የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት ይፋ እንደሚያደርግ ይጠበቃል፡፡
በግምገማ መርሃ ግብሩ ላይ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት ዶ/ር ዳምጠው ዳርዛ፣ የምርምርና ማኅበረሰብ ጉድኝት ም/ፕሬዝደንት በኃይሉ መርደኪዮስ (ተባባሪ ፕ/ር)፣ የአካዳሚክ ጉ/ም/ፕሬዝደንት ዶ/ር ዓለማየሁ ጩፋሞና ሌሎች የዩኒቨርሲቲው አመራሮችና ተመራማሪዎች ተገኝተዋል፡፡
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-
ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCAD/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA
የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት