በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በኮምፕዩተር ሳይንስና ሶፍትዌር ምኅንድስና ፋከልቲ አዘጋጅነት በተመራቂ ተማሪዎች የተሠሩ የተለያዩ የሶፍትዌር ፕሮጀክቶች ኤግዝቢሽን ሰኔ 12/2016 ዓ/ም ተካሂዷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
የቤተ-መጻሕፍትና መረጃ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር መሳይ ሳሙኤል በመክፈቻ ንግግራቸው መሰል ኤግዚቢሽን ከዚህ ቀደም በኮሮና ምክንያት ከመቋረጡ በፊት በየዓመቱ ሲደረግ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡ እንደ ዳይሬክተሩ ገለፃ በተመራቂ ተማሪዎችና በሌሎችም የተሠሩትን ሶፍትዌሮች መመልከት፣ ሥራዎችን ማድነቅ፣ መጠየቅ፣ ግንዛቤ መውሰድና ማበረታታት ይገባልም ብለዋል፡፡
የኮምፕዩተር ሳይንስና ሶፍትዌር ምኅንድስና ፋከልቲ ዲን ረ/ፕ/ር ጌታሁን ትዕግስቱ ፕሮግራሙ በተመራቂ ተማሪዎች የተሠሩ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ለዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ የሚተዋወቁበት፣ መምህራን ተማሪዎቻቸውን የሚደግፉበት እንዲሁም ተማሪዎች እርስ በእርስ ይበልጥ የሚደጋገፉበትና ይበልጥ የሚማማሩበት መድረክ መሆኑን አውስተዋል፡፡
የፋከልቲው መምህር ፕ/ር ዲፒ ሻርማ/Prof. D.P. Sharma/ በበኩላቸው ዘመኑ የመረጃና ቴክኖሎጂ ዘመን እንደመሆኑ ለአከባቢው ማኅበረሰብ፣ ለሀገርና ለቀጣይ ትውልድ ተሻጋሪ የሚሆኑ የተለያዩ ሶፍትዌሮችን ዲዛይን በማድረግ የማቅረብ ጉዳይ የሚበረታታና ይበልጥ ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት ነው ብለዋል፡፡
የ“Gamo Programing Language”፣ “Hospital Management System Web-based”፣ “Smart Path”፣ “Kelmat Art Gallery“፣ “Ext Exam”፣ “Assets Brokory”፣ “Tripmate tourist mgt System“፣ “Class scheduling system”፣ “Online job portal system for Ethiopia“፣ “Agriconect Market Integration” እና “Cofee flow” የተሰኙ ሶፍትዌሮች በኤግዚቢሽኑ ከቀረቡ የሶፍትዌር ፕሮጀክቶች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-
ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCAD/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA
የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት