ከኢትዮጵያ መንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ምክክር መድረክ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍና በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አስተባባሪነት በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ከዚህ ቀደም የመሬት መንሸራተት አደጋ በደረሰበት ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ እየተገነባ የሚገኘው  1ኛ ደረጃ ት/ቤት የደረሰበትን ደረጃ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች ሰኔ /15 2017 ዓ/ም ጎብኝተዋል።ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

በጉብኝቱ ላይ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት ዶ/ር ኢ/ር አብደላ ከማል፣ የምርምርና ትብብር ም/ፕሬዝደንት ዶ/ር ተክሉ ወጋየሁ ፣ የአስተዳርና ልማት ም/ፕሬዝደንት ፕ/ር ጳውሎስ ታደሰ ፣ የፕሬዝ ደንት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ከአምላክነሽ ደሳለኝ ፣ የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዮሐንስ ታደሠ የተገኙ ሲሆን አመራሮቹ የግንባታ ሂደቱ አሁን ላይ የደረሰበት ደረጃ አበረታች መሆኑንና የግንባታው ሥራ በፍጥነት እንዲጠናቀቅ አስፈላጊውን ድጋፍ በዩኒቨሲቲው በኩል እንደሚደርግ ቃል ገብተዋል። 

ት/ቤቱ በምክክር መድረኩ በተመደበ 10 ሚሊዮን ብር የሚሰራ ሲሆን ግንባታው ሶስት ብሎክ ያለዉና ዘጠኝ የመማሪያ ክፍሎችን የያዘ ነው። 

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት