በስፖርት አካዳሚ አዘጋጅነት በዩኒቨርሲቲው ካምፓሶች መካከል ሲካሄድ የቆየው የወንዶች እግር ኳስ ውድድር በዋናው ግቢ አሸናፊነት ታኀሣሥ 26/ 2017 ዓ/ም ፍጻሜውን አግኝቷል፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

በአባያ ካምፓስ በተደረጉ ሁለት ጨዋታዎች ፍጻሜውን ባገኘው ውድድር የዋናው ግቢ የእግር ኳስ ቡድን በሰበሰበው ሰባት ነጥብ መሪ በመሆን የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል።

በውድድሩ ላይ ተሳታፊ ለነበሩ ቡድኖች የምስክር ወረቀት የተበረከተ ሲሆን ኮከብ ተጫዋች፣ ግብ አግቢ፣  አሠልጣኝና ግብ ጠባቂ  ሆነው ላጠናቀቁ ተማሪዎች የምስክር ወረቀትና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት