የሥነ-ትምህርትና ሥነ-ባህሪ ሳይንስ ት/ቤት የባህሪ ማሻሻያ አገልግሎት መስጫ ማዕከል ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ከ “International Youth Fellowship” ጋር በመተባበር በአዕምሮ ውቅር (mindset) ዙሪያ ከኮሪያ በመጡ አሠልጣኞች ለጫሞ፣ ለዋናው ግቢ 2ኛ ዓመትና ከዚያ በላይ ለሆኑ የዩኒቨርሲቲው መደበኛ፣ ኢ-መደበኛና ለሁሉም ሪሚዲያል ተማሪዎች፣ ለባይራ አዳሪ 2ኛ ደ/ት/ቤት ተማሪዎች እና ለአርባ ምንጭ ከተማ መምህራን ከጥር 17-18/2016 ዓ.ም በዋናው ግቢ በሚገኝ አዳራሽ ሥልጠና የሚሰጥ ይሆናል፡፡
በዚህም መሠረት ሥልጠናው፡-
- ለአርባ ምንጭ ከተማ መምህራን ጥር 17/2016 ዓ.ም ከ8፡00 ጀምሮ
- ለጫሞና ዋናው ግቢ 2ኛ ዓመትና ከዚያ በላይ ለሆኑ መደበኛ ተማሪዎች፣ ለመደበኛና ኢ-መደበኛ ሪሜዲያል ተማሪዎች እና ለባይራ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ጥር 18/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ የሚሰጥ ይሆናል፡፡
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-
ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCCD/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA
የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት