በ2018 ዓ.ም. የብሔራዊ የድህረ ምረቃ መግቢያ ፈተና (National Graduate Admission Test – NGAT) ለመውሰድ ለሚያቅዱ አመልካቾች በሙሉ፣ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለፈተናው የሚያዘጋጅ የNGAT የዝግጅት ቱቶሪያል ስልጠና እንደሚሰጥ በክብር ያሳውቃል። 

1. የምዝገባ ጊዜ 

  • ከሐምሌ 14 እስከ 20 ቀን 2018 ዓ.ም. 
  • ምዝገባው በመስመር ላይ (Online) በሚቀርበው ሊንክ ይከናወናል።
    ሊንክ:  https://forms.gle/tsr2U5jKjchPqLgS6 

2. የቱቶሪያል ስልጠና ቀን 

  • ከሐምሌ 22 እስከ 24 ቀን 2018 ዓ.ም. (ረቡዕ፣ ሐሙስ እና ዓርብ) 

3. የቱቶሪያል ስልጠና ቦታ 

  • አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ዋና ግቢ 
  • ሕንፃ ቁጥር 105 (የድህረ ምረቃ ፕሮግራሞች ሕንፃ) 

4. የስልጠና መጀመሪያ ሰዓት 

  • ጠዋት 2፡30 ሰዓት 

5. የምዝገባ ክፍያ 

  • 500 (አምስት መቶ) ብር 
  • የምዝገባ ክፍያው ወደ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የውስጥ ገቢ የንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000726844163 ገቢ መደረግ አለበት። 

ማሳሰቢያ 

  • በቱቶሪያሉ ቀን የክፍያ ደረሰኙን ዋና ቅጂ (Hard Copy) ይዘው መቅረብ ይጠበቅብዎታል። 
  • የNGAT ፈተና በሐምሌ ወር መጨረሻ እንደሚሰጥ በዚህ አጋጣሚ እናሳውቃለን። 

ድህረ ምረቃ ትምህርት ቤት ዳይሬክቶሬት
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ 

የጥበብ ምንጭ!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት