አቶ ነጋልኝ ስለሺ ከአባታቸው ከአቶ ስለሺ ስሜ እና ከእናታቸው ከወ/ሮ ብሩክነሽ ብርሃኑ ሚያዝያ 08/1987 ዓ.ም በገዜ ጎፋ ወረዳ ቡልቂ ከተማ ተወለዱ፡፡ 

አቶ ነጋልኝ ስለሺ የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በቡልቂ 1ደረጃ እና በቡልቂ 2 ደረጃና መሠናዶ ት/ቤት አጠናቀዋል፡፡ አቶ ነጋልኝ ስለሺ ከሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ በሰው ሀብት አስተዳደር ዲፕሎማቸውን እና ከኒው ግሎባል ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ በማኔጅመንት የትምህርት መስክ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል፡፡

አቶ ነጋልኝ ስለሺ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሳውላ ካምፓስ ነሐሴ 25/2011 ዓ/ም የመስተንግዶና የጽዳት አስተባባሪ ሆነው በመቀጠር ሕይወታቸው እስካለፈበት ዩኒቨርሲቲውን በታማኝነት፣ በታታሪነትና በቅንነት አገልግለዋል፡፡ አቶ ነጋልኝ ባጋጠማቸው ድንገተኛ የጤና እክል በሕክምና ሲረዱ ቆይተው በተወለዱ በ29 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በአቶ ነጋልኝ ስለሺ ድንገተኛ ኅልፈተ ሕይወት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን እየገለጸ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸውና ለዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ መጽናናትን ይመኛል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ

የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCAD/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት