በ2018 የትምህርት ዘመን በትምህርት ሚኒስቴር ወደ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ለተመደባችሁ እና በ2017 ትምህርት ዘመን የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በመከታተል የማለፊያ ውጤት ላስመዘገባችሁ የቅድመ ምረቃ መደበኛ ፕሮግራም ተማሪዎች ቅበላና ምዝገባ ሐሙስና ዓርብ ጥቅምት 13 እና 14 ቀን 2018 ዓ/ም፣ ትምህርት የሚጀመረው ሰኞ ጥቅምት 17 ቀን 2018 ዓ/ም እንዲሆን ተወስኗል፡፡
በዚህ መሠረት በ2017 ትምህርት ዘመን የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በመከታተል የማለፊያ ውጤት 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች በ2017 ትምህርት ዘመን የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ትምህርት በተማራችሁበት ካምፓስ እንዲሁም በ2018 የትምህርት ዘመን በትምህርት ሚኒስቴር ወደ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች ኩልፎ (Kulfo Campus)፣ አባያ (Abaya Campus)፣ ጫሞ (Chamo Campus) እና ዋናው ግቢ (Main Campus) የተመደባችሁ ተማሪዎች በአርባ ምንጭ ከተማ በሚገኙ ኩልፎ፣ አባያ፣ ጫሞ፣ እና ዋናው ግቢ ካምፓሶች፤ ሳውላ ካምፓስ (Sawula Campus) የተመደባችሁ ተማሪዎች ደግሞ በጎፋ ዞን ሳውላ ከተማ በሚገኘው ሳውላ ካምፓስ ሬጅስትራር ማስተባበሪያ ጽ/ቤቶች በአካል እየቀረባችሁ ሪፖርት እንድታደርጉና ምዝገባ እንድትፈጽሙ እንገልጻለን፡፡
በዩኒቨርሲቲው አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች ከታች የተመለከተውን ሊንክ በመጫን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና መለያ ቁጥር በማስገባት የተመደባችሁበትን ካምፓስ ማወቅ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ሊንክ፡- https://smis.amu.edu.et/pages/check_campus_placement
ማሳሰቢያ፡-
1ኛ) ሁሉም ተማሪዎች ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕትና የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ኦርጂናልና የማይመለስ ሁለት ኮፒ እንዲሁም አንሶላ፣ የትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ በመያዝ መምጣት ይጠበቅባቸዋል፡፡
2ኛ) ከተጠቀሰው ቀን ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣ ተማሪን ዩኒቨርሲቲው አያስተናግድም፡፡
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሬጂስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-
ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA