የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ካውንስል አባላት 2018 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት የቁልፍ ተግባራት አፈጻጸም (KPI) ሪፖርት ዙሪያ ሰፊ ውይይት ሚያዝያ 29/2018 . አካሂደዋል። ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

በመድረኩ የዩኒቨርሲቲው ስትራቴጂክ ዕቅድ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሰለሞን ይፍሩ አጠቃላይ 9 ወራት አፈጻጸምን አስመልክተው ባቀረቡት ሪፖርት፤ በስርዓተ-ትምህርት ክለሳና አክሪዴቴሽን፣ በምርምርና ሕትመት ስራዎች፣ በዓለም-አቀፍ ተቋማት ጋር የመግባቢያ ስምምነት በመፍጠርና በማኅበራዊ ልማት ስራዎች የተመዘገቡ ጠንካራ አፈጻጸሞችንና መሻሻል የሚሹ ተግባራትን በዝርዝር አቅርበዋል። በተመሳሳይ የዩኒቨርሲቲው ኮሌጅና /ቤቶች ዲኖች እንዲሁም የኢንስቲትዩቶች ሳይንቲፊክ ዳይሬክተሮች የተቋሞቻቸውን ዝርዝር ሪፖርት አቅርበው ውይይት ተካሂዶባቸዋል።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት / ኢንጅነር አብደላ ከማል በውይይቱ ወቅት እንደተናገሩት፤ ግምገማው በሁሉም የሥራ ክፍሎች የታዩ ጠንካራ አፈጻጸሞችን ለማስቀጠልና ከታዩ ክፍተቶች ቀጣይ መሻሻል የሚያስችል ትምህርት ለመውሰድ ያለመ ነው። አያይዘውም ዩኒቨርሲቲው በቅርቡ ራስ ገዝ ለመሆን በሚያደርገው ጉዞ ኃላፊነት የተሞላበትና በማስረጃ ላይ የተደገፈ ትክክለኛ መረጃ በማደራጀት ረገድ ትኩረት ሊሰጥ እንደሚገባና እንደ አንድ የምርምር ዩኒቨርሲቲ አቅምን አሟጦ በመጠቀም በሕትመትና በግራንት ፕሮጀክቶች ላይ ሰፊ ሥራ መሥራት እንደሚጠበቅ አሳስበዋል።

የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝደንት / ኢንጅነር ቦጋለ ገብረማርያም በበኩላቸው፤ የተሻለና ጥራቱ የተጠበቀ ትምህርት ለመስጠት የእንግሊዝኛ ቋንቋ ማሻሻያ እና ከፍተኛ ትምህርት ዲፕሎማ ፕሮግራም (HDP) ጨምሮ የኢ-ለርኒንግ (E-Learning) እና 5 ሚሊዮን ኮደርስ ስልጠናዎች እጅጉኑ አጋዥ መሆናቸውን ገልጸዋል። በመሆኑም እነዚህ ስልጠናዎች ከምስክር ወረቀት ባለፈ ተግባር ተኮር እውቀትን መጨበጥ የሚያስችል ለውጥ ማምጣት እንዳለባቸው አጽንኦት ሰጥተዋል።

የምርምር ትብብርና ምክትል ፕሬዝደንት / ተክሉ ወጋየሁ ዩኒቨርሲቲው ወደ ራስ-ገዝነት ለመሸጋገር እያደረገ ያለውን ጥልቅ እንቅስቃሴ መረዳት አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመው፤ በቀጣይ በምርምር ሥራዎች፣ በፈጠራ ግኝቶች (Innovation) በስታርትአፕ (Startups) ንግድ ሥራዎችና በፓተንት (Patent) መብት ጥበቃ ላይ በትኩረት መሥራት እንደሚገባ አሳስበዋል። በተጨማሪም በተቀሩት የበጀት ዓመቱ ወራት የምርምር ላቦራቶሪዎች የብቃት ማረጋገጫ (Accreditation) እንዲያገኙ በትኩረት እንዲስራ አጽንዖት ሰጥተዋል።

የአስተዳደር ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝደንት ፕሮፌሰር ጳውሎስ ታደሰ የቀረበው ሪፖርት የሥራ ክፍሎችን አፈጻጸምና ዩኒቨርሲቲው ያለበትን ደረጃ በመለየት በቀጣይ በተሻለ ሁኔታ ለመሥራት አቅጣጫ የሚያሳይ መሆኑን ገልጸዋል።

የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርቱን ተከትሎ ከካውንስል አባላት በርካታ ጥያቄዎችና አስተያየቶች የተነሱ ሲሆን፤ ከሚመለከታቸው ኮሌጆች፣ ኢንስቲትዩቶችና የሥራ ክፍሎች ለቀረቡት ጥያቄዎች ሰፊ ማብራሪያና ምላሽ ተሰጥቷል።

የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮችም የቀረቡትን ግብዓቶች በማጠቃለል፣ በተቀሩት የበጀት ዓመቱ ወራት ትኩረት ሊሰጣቸው በሚገቡ አንኳር ጉዳዮች ላይ የሥራ መመሪያና የቀጣይ አቅጣጫ በማስቀመጥ ውይይቱን አጠቃልለዋል።

 

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ

የጥበብ ምንጭ!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት