የሰላም ሚኒስቴር ከትምህርት ሚኒስቴርና ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመቀናጀት በሀገር አቀፍ ደረጃ የሁለተኛና የሦስተኛ ዓመት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን አሠልጥኖ ስምሪት ለመስጠት የተዘጋጀ የክረምት ወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ ማኅበረሰብ አገልግሎት ተሳታፊዎችን ‹‹ብዝኃነት ለአብሮነት›› በሚል መሪ ቃል ከሰኔ 15 - 19 /2016 ዓ/ም የሚቆይ ሥልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
የክረምት ወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ ማኅበረሰብ አገልግሎት ተሳታፊ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን በዕውቀትና በአመለካከት እንዲበቁ በማድረግ ለሀገር ግንባታ፣ ለብሄራዊ መግባባት፣ ለሁለንተናዊ ሰላምና ዘላቂ ልማት አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ማድረግ የሥልጠናው ዋነኛ ዓላማ ሲሆን ከዚህም ባሻገር ሰላምና ኅብረ ብሄራዊ አንድነትን ማሳደግ፣ በተለያዩ የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች የሚማሩ ተማሪዎችና በአካባቢው ማኅበረሰብ መካከል አንድነትን ማጎልበት እንዲሁም ከትውልድ ቀያቸው ውጭ ያለውን ማኅበረሰብ ባህልና ቋንቋ ማስተዋወቅ የመርሃ ግብሩ ግቦች ናቸው፡፡
የሥልጠናው ይዘት የወጣቶችን የምክንያታዊ አስተሳሰብ ክሂሎት መገንባት፣ የሕይወት አመራር ክሂሎት ማስረጽ፣ የሰላም ባህል ግንባታ፣ የሀገር ግንባታና ብሄራዊ መግባባት ላይ ሚናቸውን እንዲያውቁና እንዲወጡ ማድረግ እና ዓለም አቀፍ ተለዋዋጭ ሀኔታዎችን ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-
ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCAD/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA
የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት