አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የ2017 ትምህርት ዘመን አዲስ የድኅረ ምረቃ (ማስተርስና ፒ.ኤች.ዲ.) ትምህርት ፈላጊዎች የምዝገባ እና የቅበላ ቀን ከረቡዕ መስከረም 22/2017 ዓ/ም እስከ ዓርብ መስከረም 24/2017 ዓ.ም እንዲሆን ተወስኗል፡፡
በዚሁ መሠረት በ2017 የትምህርት ዘመን የድኅረ ምረቃ ትምህርታችሁን በአንጋፋው የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለመማር የወሰናችሁ አመልካቾች በማንኛውም የመፈተኛ ማዕከል ብሔራዊ የድኅረ ምረቃ ቅበላ ፈተና (NGAT) በመውሰድ ያለፋችሁበት ውጤት መግለጫ ሰርተፍኬት፣ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሰርተፍኬት፣ የቅድመ (እና የድኅረ ምረቃ) ትምህርት ማስረጃ ኦሪጂናልና የማይመለስ ሁለት ኮፒ በመያዝ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሬጂስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት ሕንጻ ቢሮ ቁጥር 210 እና 211 እየቀረባችሁ እንድትመዘገቡ ጥሪያችንን እያስተላለፍን ሰኞ መስከረም 27/2017 ዓ.ም ትምህርት የሚጀመር መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ማሳሰቢያ፡- ለድኅረ ምረቃ ትምህርት ፈላጊዎች በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ድኅረ ምረቃ ት/ቤት በኩል የቀረቡ ገጸ በረከቶችን ከዚህ ማስታወቂያ ጋር እንዲደርሳችሁ የተደረገ መሆኑን እንዲሁም የቅድመ ምረቃ (የድኅረ ምረቃ) ትምህርት ማስረጃ ኦፊሻል በፖስታ ሳጥን ቁጥር ወይም በኢሜይል አድራሻዎች
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት