የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ድኅረ ምረቃ ት/ቤት በ2017 ዓ.ም በተለያዩ ፕሮግራሞች ትምህርታቸውን ለጀመሩ አዲስ ገቢ ተማሪዎች የትምህርት ቤቱን ሕግ፣ ደንብና አጠቃላይ የተቋሙን ነባራዊ ሁኔታ አስመልክቶ ጥቅምት 29/2017 ዓ.ም ገለጻ ሰጥቷል፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ
በዕለቱ ምዝገባ፣ የሬጂስትራር፣ መኝታ፣ ምግብና ሌሎች አገልግሎቶች እንዲሁም በትምህርት ቤቱ ውስጥ ያሉ መመሪያና ደንቦች እና ተማሪዎቹ ከሚወስዱት ትምህርት ጋር የተያያዙ የክፍያ ሥርዓቶች አስመልክቶ ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡
የድኅረ ምረቃ ት/ቤት ዳይሬክተር ዶ/ር ተክሉ ወጋየሁ በትምህርት ቤቱ ለ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ላለፉት አራት ወራት ያህል የዝግጅት ሥራዎች ሲከናወኑ መቆየታቸውን ተናግረዋል፡፡ በዩኒቨርሲቲው ለ2017 የትምህርት ዘመን 879 ተማሪዎች ሀገራዊ የድኅረ ምረቃ የመግቢያ ፈተና መውሰዳቸውን የጠቀሱት ዳይሬክተሩ ከእነዚህ መካል 41 የ3ኛ እና 99 የ2ኛ ዲግሪ በአጠቃላይ 140 አዲስ ገቢ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ተዘጋጅተናል ብለዋል፡፡ ከዚህ ቀደም ተቋርጦ የነበረው የክረምት መርሃ ግብር ከትምህርት ሚንስቴር በተሰጠው አቅጣጫ መሠረት እንዲቀጥል መደረጉንም ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡
የድኅረ ምረቃ ተማሪዎች ለግራንድ ፕሮጀክቶች በሚሰጠው 1.75 ሚሊዬን ብር የመሳተፍ እንዲሁም በተለይ የ3ኛ ዲግሪ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው በሚኖሩ የምርምር ፕሮጀክቶች ውስጥ የሚካሄድ ውድድርን ማለፍ ከቻሉ ወንዶች 175 ሺህ ሴቶች 180 ሺህ ብር የምርምር መሥሪያ በጀት የማግኘት ዕድል እንዳላቸውም ዶ/ር ተክሉ ጠቅሰዋል፡፡ በተጨማሪም አካል ጉዳተኞች ተመጣጣኝ በሆነ መልኩ የትምህርት ክፍያ፣ የመኝታና የምግብ አገልግሎት ድጎማዎችን ማግኘት እንደሚችሉም ዳይሬክተሩ አመላክተዋል፡፡
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-
ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCAD/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA
የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት