በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ በሂሳብ ት/ክፍል በ‹‹Numerical Analysis›› ትምህርት ፕሮግራም   የ3ኛ ዲግሪ ትምህርቱን ሲከታተል የቆየው ዕጩ ዶ/ር ዘርይሁን ኢብራሂም የመመረቂያ ጽሑፍ ታኅሣሥ 23/2017 ዓ.ም የውጭና የውስጥ ገምጋሚዎች እንዲሁም አማካሪዎች በተገኙበት ቀርቦ ተገምግሟል፡፡ የመመረቂያ ጽሑፉም አስፈላጊውን መስፈርት በማሟላቱ በአማካሪ ቦርዱ ተቀባይነት አግኝቶ ጸድቋል፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

ዕጩ ዶ/ር ዘርይሁን ኢብራሂም የመጀመሪያ ዲግሪውን ከጅማ ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም 2ኛ ዲግሪውን ከሐሮማያ ዩኒቨርሲቲ በሂሳብ ትምህርት ያገኘ ሲሆን የ3ኛ ዲግሪ ትምህርቱን ከ2012 ዓ/ም ጀምሮ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሲከታተል ቆይቶ የመመረቂያ ጽሑፉን ‹‹Numerical Treatment of Singularly Perturbed Delay Parabolic Convection-Diffusion Equation›› በሚል ርእስ አከናውኗል፡፡

የዕጩ ዶ/ር ዘርይሁን ኢብራሂም ውጤት ለዩኒቨርሲቲው ሴኔት ቀርቦ ተቀባይነት ሲያገኝ የሚመረቅ ይሆናል፡፡ 

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት