በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ባዮሎጂ ት/ክፍል በ‹‹Biodiversity Conservation and Management›› የትምህርት ፕሮግራም የ3ኛ ዲግሪ ትምህርቱን ሲከታተል የቆየው የዕጩ ዶ/ር ኢያሱ ጫማ የመመረቂያ ጽሑፍ ግንቦት 13/2016 ዓ/ም የውጭና የውስጥ ገምጋሚዎች እንዲሁም አማካሪዎች በተገኙበት ቀርቦ ተገምግሟል፡፡ የመመረቂያ ጽሑፉ አስፈላጊውን መስፈርት በማሟላቱ በአማካሪ ቦርዱ ጸድቋል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
ዕጩ ዶ/ር ኢያሱ ጫማ የመጀመሪያ ዲግሪውን በ‹‹Biology›› እና ሁለተኛ ዲግሪውን በ‹‹Dryland Biodiversity›› ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አግኝቷል፡፡ የ3ኛ ዲግሪ ትምህርቱን በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በ‹‹Biodiversity Conservation and Management›› በ2010 ዓ/ም የጀመረው ዕጩ ዶ/ር ኢያሱ የመመረቂያ ምርምሩን ‹‹Plant Communities, Socioeconomic Values, and Carbon Stock Potential of Forest Patches in Wolaita, Southern Ethiopia›› በሚል ርዕስ አከናውኗል፡፡
ዶ/ር ገመዶ ዳሎ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና ዶ/ር ዳንኤል ፍታሞ ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የመመረቂያ ጽሑፍ የውጪ ገምጋሚ ሲሆኑ ዶ/ር ሽቴ ጋተው ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የውስጥ ገምጋሚ ሆነው ተገኝተዋል፡፡ በግምገማ መርሃ ግብሩ የውስጥና የውጪ ገምጋሚዎችን ጨምሮ የኮሌጅ ዲኖች፣ የትምህርት ክፍል ኃላፊዎች፣ የዘርፉ መምህራንና የድኅረ ምረቃ ተማሪዎች ታድመዋል፡፡
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-
ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCAD/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA
የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት