በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ማኔጅመንት ትምህርት ክፍል በ‹‹Human Resource Management›› ትምህርት ፕሮግራም የ3ኛ ዲግሪ ትምህርቱን ሲከታተል የቆየው ዕጩ ዶ/ር አቤል ተወልደ የመመረቂያ ጽሑፍ ጥቅምት 7/2018 ዓ/ም የውጭና የውስጥ ገምጋሚዎች እንዲሁም አማካሪዎች በተገኙበት ቀርቦ ተገምግሟል። የመመረቂያ ጽሑፉ አስፈላጊውን መስፈርት በማሟላቱ በአማካሪ ቦርዱ ተቀባይነት አግኝቶ ጸድቋል፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

ዕጩ ዶ/ር አቤል ተወልደ የመጀመሪያ ዲግሪውን ከጅማ ዩኒቨርሲቲ በቢዝነስ ማኔጅመንት እንዲሁም 2ኛ ዲግሪውን ከአዳማ ዩኒቨርሲቲ በቢዝነስ አድሚንስትሬሽን አግኝቷል፡፡

ዕጩ ዶ/ር አቤል የ3ኛ ዲግሪ ትምህርቱን በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በ‹‹Human Resource Management›› ትምህርት ክፍል ሲከታተል ቆይቶ የመመረቂያ ጽሑፉን ‹‹Thee Effect of Work Force Diversity on Organizational Performance with Mediation Role of Workplace Ethics and Organizational Conflict: Emphasis on Food and Beverage Firms in Ethiopia›› በሚል ርእስ ሠርቷል፡፡

የዕጩ  ዶ/ር  አቤል ተወልደ ውጤት ለዩኒቨርሲቲው ሴኔት ቀርቦ የሚመረቅ ይሆናል፡፡

 

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት