በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በ‹‹Computing and Software Engineering›› ፋከልቲ በ‹‹Computing and Information Technology›› የትምህርት ፕሮግራም የ3ኛ ዲግሪ ትምህርቱን ሲከታተል የቆየው ዕጩ ዶ/ር አስቻለው አረጋ የመመረቂያ ጽሑፍ ጥቅምት 7/2018 ዓ/ም የውጭና የውስጥ ገምጋሚዎች እንዲሁም አማካሪዎች በተገኙበት ቀርቦ ተገምግሟል። የመመረቂያ ጽሑፉ አስፈላጊውን መስፈርት በማሟላቱ በአማካሪ ቦርዱ ተቀባይነት አግኝቶ ጸድቋል፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

ዕጩ ዶ/ር አስቻለው አረጋ ከአልፋ ኮሌጅ ሐዋሳ ቅርንጫፍ በ‹‹Computer Application›› በዲፕሎማ የተመረቀ ሲሆን የመጀመሪያ ዲግሪውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ‹‹Information System›› እንዲሁም 2ኛ ዲግሪውን ከጃፓን ኮቤ ኢንስቲትዩት/Kobe Institute of Computing/ በ‹‹Information System›› አግኝቷል፡፡

ዕጩ ዶ/ር አስቻለው የ3ኛ ዲግሪ ትምህርቱን በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በ‹‹Computing and Information Technology›› የትምህርት ፕሮግራም ሲከታተል ቆይቶ የመመረቂያ ጽሑፉን ‹‹Developing a Cloud-Enabled Smart and Sustainable Healthcare Information System Service Model for Ethiopia›› በሚል ርእስ ሠርቷል፡፡

የዕጩ  ዶ/ር አስቻለው አረጋ ውጤት ለዩኒቨርሲቲው ሴኔት ቀርቦ የሚመረቅ ይሆናል፡፡

 

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት