በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በማኅበራዊ ሳይንስና ሥነ ሰብ ኮሌጅ በ"Geography and Environmental Studies" ትምህርት ክፍል በ"Environment and Natural Resource Management" ትምህርት ፕሮግራም የ3ኛ ዲግሪ ትምህርቱን ሲከታተል የቆየው የዕጩ ዶ/ር ጀምበር በክረ የመመረቂያ ጽሑፍ ኅዳር 21/2017 ዓ.ም የውጭና የውስጥ ገምጋሚዎች እንዲሁም አማካሪዎች በተገኙበት ቀርቦ ተገምግሟል፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

የመመረቂያ ጽሑፉም አስፈላጊውን መስፈርት በማሟላቱ በአማካሪ ቦርዱ ተቀባይነት አግኝቶ ጸድቋል፡፡ 

ዕጩ ዶ/ር ጀምበር በክረ የመጀመሪያ ዲግሪውን ከመዳ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ በ"Geography & Environmental Studies" እንዲሁም የ2ኛ ዲግሪውን ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከ "Geography and Environmental Study" ትምህርት ክፍል በ "Land Use Management" ያገኘ ሲሆን  የ3ኛ ዲግሪውን በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሲከታተል ቆይቶ የመመረቂያ ጽሑፉን "LAND USE /LAND COVER DYNAMICS, ECOSYSTEM SERVICE VALUTION AND FOREST DESTRUCTION IN WESTERN ETHIOPIA" በሚል ርእስ አከናውኗል፡፡

የዕጩ ዶ/ር ጀምበር በክረ ውጤት ለዩኒቨርሲቲው ሴኔት ቀርቦ ተቀባይነት ሲያገኝ የሚመረቅ ይሆናል፡፡


አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCCD/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት