በአርባ ምንጭ ውኃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በ ‹‹Hydraulic & Water Resources Engineering›› ፋከልቲ በ‹‹Hydraulic Engineering›› ትምህርት ፕሮግራም የ3ኛ ዲግሪ ትምህርቱን ሲከታተል የቆየው ዕጩ ዶ/ር መስፍን ረታ የመመረቂያ ጽሑፍ ጥቅምት 15/2017 ዓ.ም የውጭና የውስጥ ገምጋሚዎች እንዲሁም አማካሪዎች በተገኙበት ቀርቦ ተገምግሟል፡፡ የመመረቂያ ጹሑፉ አስፈላጊውን መስፈርት በማሟላቱ በአማካሪ ቦርዱ ተቀባይነት አግኝቶ ጸድቋል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
ዕጩ ዶ/ር መስፍን ረታ የመጀመሪያ ዲግሪውን ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በሃይድሮሊክና ውኃ ሀብት ምኅንድስና እንዲሁም 2ኛ ዲግሪውን ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በሃይድሮሎጂ ያገኘ ሲሆን የ3ኛ ዲግሪ ትምህርቱን በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሲከታተል ቆይቶ የመመረቂያ ጹሑፉን ‹‹Integrated Water Balance & Watershed Health Assessment Under Existing Water Use & Future Development Plans in Weyib Watershed, Ethiopia›› በሚል ርእስ አከናውኗል፡፡
የዕጩ ዶ/ር መስፍን ረታ ውጤት ለዩኒቨርሲቲው ሴኔት ቀርቦ ተቀባይነት ሲያገኝ የሚመረቅ ይሆናል፡፡
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-
ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCAD/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA
የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት