በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በማኅበራዊ ሳይንስና ሥነ ሰብ ኮሌጅ በ"Geography and Environmental Studies" ትምህርት ክፍል  በ"Environment and Natural Resource Management" ትምህርት ፕሮግራም የ3ኛ ዲግሪ ትምህርቱን ሲከታተል የቆየው ዕጩ ዶ/ር ዘውዴ ሱፋራ የመመረቂያ ጽሑፍ ኅዳር 13/2017 ዓ.ም የውጭና የውስጥ ገምጋሚዎች እንዲሁም አማካሪዎች በተገኙበት ቀርቦ ተገምግሟል፡፡ የመመረቂያ ጽሑፉም አስፈላጊውን መስፈርት በማሟላቱ በአማካሪ ቦርዱ ተቀባይነት አግኝቶ ጸድቋል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

ዕጩ ዶ/ር ዘውዴ ሱፋራ የመጀመሪያ ዲግሪውን ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በ"Geography and Environmental Study" እንዲሁም የ2ኛ ዲግሪውን ከዚሁ  ዩኒቨርሲቲ ከ "Geography and Environmental Study" ትምህርት ክፍል በ "Physical Geography" ያገኘ ሲሆን  የ3ኛ ዲግሪውን በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሲከታተል ቆይቶ የመመርቂያ ጽሑፉን"CLIMATE VARIABILITY AND LAND USE/COVER CHANGE IMPLICATIONS FOR RURAL HOUSEHOLD FOOD SECURITY AROUND GHIBE III DAM, SOUTHERN ETHIOPIA"  በሚል ርእስ አከናውኗል፡፡

የዕጩ ዶ/ር ዘውዴ ሱፍራ  ውጤት ለዩኒቨርሲቲው ሰኔት ቀርቦ ተቀባይነት  ሲያገኝ የሚመረቅ ይሆናል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ

የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት