በ2015 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ወስዳችሁ በግል የማካካሻ ትምህርት በ2016 የትምህርት ዘመን አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለመማር የተመዘገባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ጥር 6/2016 ዓ.ም፣ የትምህርት ክፍያ የምትከፍሉት ከጥር 6 - 7/2015 ዓ.ም እና ትምህርት የሚጀመረው ጥር 8/2016 ዓ.ም ስለሆነ በግል ለመማር የተመዘገባችሁ ተማሪዎች አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ በአካል ተገኝታችሁ ትምህርት እንድትጀምሩ ዩኒቨርሲቲው ያሳውቃል፡፡
ማሳሰቢያ፡-
ከተጠቀሰው ቀን ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣ ተማሪን ዩኒቨርሲቲው የማያስተናግድ መሆኑን በጥብቅ ያሳውቃል፡፡
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተከታታይና ርቀት ትምህርት ኮሌጅ
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-
ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCCD/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA
የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት