የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተከታታይና ርቀት ትምህረት ኮሌጅ በማታው የትምህርት ፕሮግራም መስፈርቱን የሚያሟሉ አዲስ አመልካቾችን በአርባ ምንጭ እና በሳውላ ማዕከል ተቀብሎ በ ‹‹Remedial›› ፕሮግራም ከ2017 ዓ.ም አንደኛ ሴሚስቴር ጀምሮ ማሠልጠን ይፈልጋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው በ2016 ዓ/ም የሀገር አቀፍ ማጠቃለያ ፈተና ወስዳቸሁ በግል ‹‹Remedial›› መግቢያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ምዝገባ መጀመሩን እየገለጽን በኤክስቴንሽን ፕሮግራም የሪሜድያል (Extension Remedial) ተማሪዎች እንደተፈተናችሁት የትምህርት አይነት ብዛት 31% በትምህርት ሚኒስቴር መቁረጫ ነጥብ ያላችሁ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
1. የተፈጥሮ ሳይንስ 31%*700=217 እና ከዝያ በላይ
2. የተፈጥሮ ሳይንስ 31%*600=186 እና ከዝያ በላይ
3. ማኀበራዊ ሳይንስ 31%*600=186 እና ከዝያ በላይ ይሆናል
የሚያስፈልጉ መረጃዎች
የማይመለስ አንድ ክላሰር/ዶሲ/፣ 1 ጉርድ ፎቶ ግራፍና የማመልከቻ ክፍያ ብር 50.00 /ሃምሳ ብር/ በዩኒቨርሲቲው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000021480502 ገቢ የተደረገበት ደረሰኝ ከትምህርት ማስረጃ ጋር በማያያዝ::
የማመልከቻ ቦታና የምዝገባ ጊዜ
የማመልከቻ ቦታ:-
አርባ ምንጭ፡- አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ነጭ ሣር ካምፓስ የተከታታይና ርቀት ትምህርት ኮሌጅ ሬጅስትራር ጽ/ቤት እንዲሁም በዋናው ግቢ የሬጅስትራር ጽ/ቤት
ሳውላ- ሳውላ ካምፓስ ሬጅስትራር ጽ/ቤት
የምዝገባ ጊዜ፡-ጥቅምት 10/2017 እስከ ጥቅምት 20/2017 ይሆናል::
ትምህርት የሚጀመርበት ጊዜ-በውስጥ ማስታወቂያ ይገለጻል
ለተጨማሪ መረጃ፡- 046-181-5468 እና 046-181-0228 ወይም በዩኒቨርሲቲያችን ድረ ገጽ /www.amu.edu.et/ ማግኘት ይችላሉ፡፡
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተከታታይና ርቀት ትምህርት ኮሌጅ
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-
ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCAD/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA
የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት