የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ በ2017 ዓ.ም በኮሌጁ ለተመደቡ የሪሚዲያል ተማሪዎች ታኅሣሥ 4/2017 ዓ.ም ኦሬንቴሽን ሰጥቷል፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ
የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ቴዎድሮስ ብርሃኑ በመክፈቻ ንግግራቸው ተማሪዎች የተሰጣቸውን መልካም ዕድል ሳያባክኑ በአግባቡ ሊጠቀሙ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ ተማሪዎች በኮሌጁ የሚኖራቸው ቆይታ በ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ሲማሩ የቆዩትን ትምህርት የመከለስ ሥራ እንደሚሰራና ቆይታቸው ስኬታማ እንዲሆን ኮሌጁ የሚጠቅበትን እንደሚወጣ እንዲሁም ከተማሪዎቹ የላቀ ትጋት እንደሚጠበቅ አስገንዝበዋል፡፡
የሪሚዲያል ፕሮግራም ወደ ዩኒቨርሲቲ ለመግባት የተሰጠ ሁለተኛ ዕድል መሆኑን የገለጹት የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ም/ዲን አቶ አድማሱ ጣሰው በበኩላቸው ተማሪዎች በሚኖራቸው የግቢ ቆይታ ቤተሰባዊ ግንኙነትን በማዳበር መብትን መጠቀምና ግዴታን መወጣት እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲ ብዝሃ ማንነት ያለበት ተቋም በመሆኑ ተባብሮና ተቻችሎ የመኖር ባህልን ማዳበር ከተማሪዎቹ እንደሚጠበቅም ም/ዲኑ አክለዋል፡፡
በመርሃ ግብሩ ላይ ሀገር አቀፍ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የዲሲፕሊን መመሪያዎች እና የተማሪዎች አገልግሎት ዘርፍ እንዲሁም የተማሪዎች ኅብረት የሚሰጡት አገልግሎት ላይ ሰፋ ያለ ማብራሪያ የቀረበ ሲሆን በዕለቱ የኮሌጁን ዲን ጨምሮ ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች፣ የተማሪዎች ኅብረት ፕሬዝደንትና አባላት ተሳትፈዋል፡፡
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-
ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA
የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት