የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የጋራ ኮርሶች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በዋናው ግቢ ለሚገኙ የሪሜዲያል ተማሪዎች ኦንላይን ፈተና አሰጣጥን አስመልክቶ ግንቦት 29/2016 ዓ/ም ገለጻ አድርጓል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝደንት ዶ/ር ዓለማየሁ ጩፋሞ እንደ ሀገር በተለዩ ዩኒቨርሲቲዎች ለመጀመሪያ ጊዜ ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በኦንላይን እንደሚሰጥ ተናግረው ተማሪዎች ገለጻውን በሚገባ ተከታትለው በሚሰጣቸው ጊዜያዊ መለያ ቁጥር በመጠቀም እስከ ፈተናው ቀን ድረስ በዩኒቨርሲቲው ባሉት የኮምፕዩተር ላቦራቶሪዎች በግልም በቡድንም በመለማመድ ራሳቸውን ለፈተናው እንዲያዘጋጁ አሳስበዋል፡፡
የገለጻው ዓላማ የተማሪዎችን ኦንላይን የኮምፕዩተር አጠቃቀም ክሂሎት ማሳደግ፣ ፈተናው በጊዜ የተገደበ በመሆኑ የጊዜ አጠቃቀማቸውን እንዲያሻሻሉ ማድረግና በቀጣይ ሀገር አቀፍ ፈተና ላይ የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ ማስቻል መሆኑን የውኃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የጋራ ኮርሶች ማስተባባሪ ጽ/ቤት ኃላፊ መ/ር መልካሙ አጠቃ ገልጸዋል፡፡
በዩኒቨርሲቲው የሪሜዲያል ተማሪ የሆነው አንዷለም አንተነህ በሰጠው አስተያየት የተሰጠው ገለጻ እጅግ ጠቃሚ መሆኑን ተናግሮ ጊዜውን በአግባቡ በመጠቀም በግልም ሆነ ከጓደኞቹ ጋር ልምምድ በማድረግ የተሻለ ውጤት ለማምጣት መዘጋጀቱን ተናግሯል፡፡
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-
ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCAD/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA
የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት