የምርምርና ትብብር ም/ፕሬዝደንት በሥሩ ከሚገኙ የሥራ ክፍል ኃላፊዎች ጋር እንዲሁም ዋና ዳይሬክቶሬቶች በሥራቸው ከሚገኙ ዳይሬክተሮችና አስተባባሪዎች ጋር በ2017 ዓ.ም ተግባራዊ የሚደረግ የቁልፍ ተግባራት አፈጻጸም ውል (KPI) ጥር 16/2017 ዓ.ም ተፈራርመዋል፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ
በዕለቱ የምርምርና ትብብር ም/ ፕሬዝደንት ዶ/ር ተክሉ ወጋየሁ ከምርምርና ልማት ካውንስል አባላት ጋር በ2017 ዓ/ም የ2ኛ ሩብ ዓመት አፈጻጸም፣ በተመዘገቡ ስኬቶችና በታዩ ተግዳሮቶች ላይ ውይይት አካሂደዋል፡፡
የምርምና ትብብር ም/ፕሬዝደንት ዶ/ር ተክሉ ወጋየሁ እንደገለጹት ፈጻሚ አካላት ተቆጥሮና ተለክቶ የተሰጣቸውን ቁልፍ ተግባራት ለመፈጸም በትኩረት መሥራት እንዳለባቸውና በቀጣይም ከግለሰብ ፈጻሚዎች ጋር ውል በመግባት ለዕቅዶቹ መሳካት በትጋት መሥራት እንደሚገባቸው አሳስበዋል።
በውይይት መድረኩ ላይ ስምንት ዋና ዋና አጀንዳዎች የተነሡ ሲሆን በሦስት ወራት ውስጥ የተሠሩ ሥራዎች፣ የተመዘገቡ ስኬቶችና የታዩ ተግዳሮቶች ላይ ምክክር ተደርጎ መፍትሔዎች መቀመጣቸውን ዶ/ር ተክሉ ገልጸዋል፡፡
ከዚህም ባሻገር በሁሉም ኮሌጆችና የምርምር ማእከላት ያሉ ያልተጠናቀቁ ፕሮጀክቶች፣ የሚገኙበት ደረጃ እንዲሁም ፕሮጀክቶቹን ለማጠናቀቅ የሚያስፈልገው ጊዜና ገንዘብ ሌላኛው ውይይት የተደረገበት ርእሰ ጉዳይ መሆኑን የገለጹት ዶ/ር ተክሉ ባልተጠናቀቁ የምርምር ፕሮጀክቶች ዙሪያ ያሉ መረጃዎች ባጭር ጊዜ ውስጥ ቀርበው ፕሮጀክቶቹን ለማጠናቀቅ እንዲሠራ አቅጣጫ መቀመጡን አውስተዋል።
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-
ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA
የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት