የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፕሬዝደንቶች፣ ሌሎች የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተወካዮችና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የኢትዮጵያ ምርምር ዩኒቨርሲቲዎች ፎረም በጎንደር ዩኒቨርሲቲ በዛሬው ዕለት በይፋ ተመሥርቷል።ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ
ፎረሙ የምርምር ዩኒቨርሲቲዎች በብሔራዊ ልማት፣ ፈጠራ እና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት መድረክ የሚተባበሩበት እና በጋራ የሚሠሩበት የመተባበር እና ትስስር መድረክ ሆኖ የሚያገለግል ነው። የፎረሙ አባል ተቋማት በዋናነት በምርምር፣ በድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች፣ በመምህራን ልማት እና በፈጠራ ማዕቀፎች ላይ በትብብር የሚሰሩ ይሆናል።
የምርምር አቅምን ማሳደግ፣ ለብሔራዊ ፖሊሲዎች ግብዓት ማቅረብ፣ የትብብር ማዕቀፎችን ማጠናከር፣ የምርምር መሠረተ ልማቶችን በጋራ መጠቀም፣ የእውቀት ሽግግርን ማፋጠን እና ዓለም አቀፋዊ ተፅዕኖን ማሳደግ የፎረሙ ዋነኛ ዓላማዎች መሆናቸው በምሥረታው ወቅት ተገልጿል።
በፎረሙ ምሥረታ ላይ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንት ዶ/ር ኢ/ር አብደላ ከማልን ጨምሮ የሌሎች ምርምር ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዝደንቶች፣ ከፍተኛ አመራሮችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-
ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA
የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት