በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሳውላ ካምፓስ የክረምት ተማሪ የሆነችው አስቴር ዮሴፍ ከእናቷ ወ/ሮ ወርቅነሽ ዋንባራ እና ከአባቷ ከአቶ ዮሴፍ አኔቦ በጎፋ ዞን ዛላ ወረዳ ጋይላ ቀበሌ መስከረም 02/1988 ዓ/ም ተወለደች፡፡

የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቷን በጋይላ እና ኩሲቲ ሙሉ 1 ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንዲሁም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን በሳውላ 2 ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት ተከታትላለች፡፡ በ2009 ዓ/ም ከአርባ ምንጭ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ በመምህርነት ሙያ በዲፕሎማ የተመረቀችው ተማሪ አስቴር ከ2010 ዓ/ም ጀምሮ በጎፋ ዞን በሚገኙ የተለያዩ ት/ቤቶች የጎፍኛ ቋንቋ መምህርት በመሆን ስታገለግል ቆይታለች፡፡ 

ተማሪ አስቴር ከ2013 ዓ/ም ጀምሮ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሳውላ ካምፓስ በጎፍኛ ቋንቋና ሥነ ጽሑፍ ት/ክፍል የመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርቷን በመከታተል የ3 ዓመት ተማሪ ነበረች፡፡

ተማሪ አስቴር ባለ ትዳርና የአንድ ወንድና የአንዲት ሴት ልጅ እናት ስትሆን ባደረባት ድንገተኛ ሕመም ምክንያት ነሐሴ 20/2016 ዓ/ም በ28 ዓመቷ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች፡፡

ዩኒቨርሲቲው በተማሪ አስቴር ዮሴፍ ኅልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን እየገለጸ ለሟች ቤተሰቦች፣ ወዳጅ ዘመዶች፣ ጓደኞችና የሥራ ባልደረቦች እንዲሁም ለዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ መጽናናትን ይመኛል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ

የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCAD/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት