የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሳውላ ካምፓስ በ2018 ዓ/ም የትምህርት ዘመን በካምፓሱ ለተመደቡ አዲስ ገቢ የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች የእንኳን ደኅና መጣችሁ እና የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሐ ግብር አካሂዷል፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

የካምፓሱ ኃላፊ አቶ ዘለቀ ዶሳ የዩኒቨርሲቲ ቆይታ ትልቅ ኃላፊነት፣ ፅናት እና ጥንቃቄ የሚጠይቅ መሆኑን ተናግረው ተማሪዎች ለትምህርታቸው ትልቅ ቦታ በመስጠት ለሀገር የሚያገለግሉ ብቁ ባለሙያዎች ለመሆን በትጋት እንዲሠሩ አሳስበዋል።

የካምፓሱ አካዳሚክ እና ምርምር ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ሜጊሶ በበኩላቸው ተማሪዎች በካምፓሱ በሚኖራቸው ቆይታ ጥራት ያለው ዕውቀት እና ክሂሎት እንዲጨብጡ ካምፓሱ ዝግጁ መሆኑን ገልጸው ከስሜታዊነት ይልቅ ምክንያታዊነትን ባህልን እንዲያዳብሩ መክረዋል።

የሳውላ ካምፓስ የተማሪዎች አገልግሎት ም/ዲን አቶ ድረስ ዱማዬ ስለ ካምፓሱ አጠቃላይ የተማሪዎች አገልግሎቶች (መኝታ፣ ምግብ ቤት፣ ሕክምና) እንዲሁም ተማሪዎች ሊያከብሯቸው ስለሚገቡ የዩኒቨርሲቲ ሕገ ደንቦችና የዲሲፕሊን መመሪያዎች ላይ ዝርዝር ማብራሪያ ሰጥተዋል። አቶ ድረስ ተማሪዎች ከደንብ ውጭ ከሆኑ እንቅስቃሴዎች ከመሳተፍ እንዲርቁም አጥብቀው አሳስበዋል።

የካምፓሱ ተባባሪ ሬጅስትራር አቶ መሪይሁን ታፈሰ የኮርስ ምዝገባ ሂደት፣ የፈተና አሰጣጥ ሥርዓት፣ የክሬዲት ሰዓት ስሌት እና ተማሪዎች ትምህርታቸውን በስኬት ለማጠናቀቅ ሊከተሏቸው የሚገቡ መመሪያዎች ዙሪያ ሰፊ ገለጻ ያቀረቡ ሲሆን የፍሬሽማን አስተባባሪ የሆኑት አቶ ዳንኤል አዘዘ በተለይ ለአንደኛ ዓመት ተማሪዎች በሚሰጡት የፍሬሽማን ኮርሶች  ዙሪያ ግንዛቤ በመስጠት ተማሪዎች ኮርሶቹን በብቃት እንዲያጠናቅቁ የሚረዳ ምክር ለግሰዋል።

በመርሐ ግብሩ ላይ የተማሪዎች ኅብረትና የሰላም ፎረም ኃላፊዎች ተገኝተው ገለጻ ያደረጉ ሲሆን አደረጃጀቶቹ በማንኛውም ጊዜ ለተማሪዎች ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።


ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት