የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዩኒቨርሲቲዎች ፎረም አባል በሆኑት አርባ ምንጭ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ጂንካና ዲላ ዩኒቨርሲቲዎች ተግባራዊ የሚደረግ በክልሉ የሚገኙ ሕዝቦችን ሀገር በቀል ዕውቀቶች መሰነድን ዓላማ ያደረገ የትብብር ፕሮጀክት ዛሬ የካቲት 3/2018 / የዩኒቨርሲቲዎቹ የሥራ ኃላፊዎችና ተመራማሪዎች፣ ከክልሉ ባህልና ስፖርት ቢሮ፣ ትምህርት ቢሮ እንዲሁም ብሔረሰቦች ምክር ቤት የተወጣጡ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች በተገኙበት በይፋ ተጀምሯል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

በዕለቱ አዲስ የተጀመረውን ፕሮጀክት በይፋ ከማስጀመር ባሻገር አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የመጥፋት አደጋ በተጋረጠባቸው የኦንጎታ እና ኩየጉ ቋንቋዎችንና ሌሎች ሀገር በቀል ዕውቀቶችን መሰነድ ዙሪያ ያከናወናቸው የምርምር ሥራዎች ውጤቶች ቀርበው በባለድርሻ አካላት ተገምግመዋል፡፡

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት / / አብደላ ከማል ዩኒቨርሲቲው እንደ ምርምር ዩኒቨርሲቲ በዋናነት ለሀገርና ለማኅበረሰብ የሚጠቅሙ ምርምሮችን ማከናወን ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ እንደ ሀገር ያሉንን ሀገር በቀል ዕውቀቶች ሰንዶ ማስቀመጥና በሳይንሳዊ ምርምር አስደግፎ ጥቅም ላይ የማዋል ጉዳይ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ያሳሰቡት ፕሬዝደንቱ  ሀገር በቀል ዕውቀቶችና ቋንቋዎች እንዳይጠፉ ለማስቻል ዩኒቨርሲቲው በትኩረት እየሰራ መሆኑንም አውስተዋል፡፡ እንደ ሀገር ከሀገር በቀል ዕውቀቶች ማግኘት የሚገባንን ጥቅም እያገኘን አይደለም ያሉት ፕሬዝደንቱ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሚገኙ ዘርፈ ብዙ ሀገር በቀል ዕውቀቶችን ለመሰነድ በዛሬው ዕለት ይፋ የተደረገው ፕሮጀክት ስኬታማ እንዲሆን ዩኒቨርሲቲው የሚጠበቅበትን ይወጣል ብለዋል፡፡

የምርምርና ትብብር /ፕሬዝደንት / ተክሉ ወጋየሁ የሀገር በቀለ ዕውቀት ስነዳ በዚህ ወቅት እንደ ሀገር ከሚፈለጉ  ቁልፍ መረጃዎች መካከል አንዱ መሆኑን ገልጸዋል። አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲም ለሀገር በቀል ዕውቀት ስነዳና ልማት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ያነሱት / ተክሉ የኣንጎታ እና የኩይጉ ቋንቋዎችን መሠረት አድርገው እየተከሆኑ የሚገኙ ሀገር በቀል ዕውቀትን መሠረት ያደርጉ የምርምር ፕሮጀክቶችን እንዲሁም የጋሞ ዱቡሻ ዋጋን በዓለም ቅርስነት ለማስመዝገብ የተከናወነውን የምርምር ሥራ ለአብነት አንስተዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዩኒቨርሲቲዎች ፎረም ከተመሰረት ጊዜ ጀምሮ የተለያዩ ክልላዊ ብሎም ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸው የትብብር ሥራዎችን እየሰራ መሆኑን የገለጹት /ፕሬዝደንቱ በክልሉ የሚገኙ ሀገር በቀል ዕውቀቶችን ለመሰነድ ይፋ የተደረገው ፕሮጀክት በዚሁ ፎረም አስተባባሪነት በአራቱ ዩኒቨርሲቲዎች የፋይናንስ፣ የሰው ኃይልና የግብአት ትብብር የሚሰራ መሆኑንም ተናግረዋል። ይህም ከተበጣጠሱ ተናጠላዊ ሥራዎች በመውጣት ፋይዳቸው ከክልል አልፈው በሀገር ደረጃ ተጽእኖ መፍጠር የሚያስችሉ ተግባራትን በጋራ ሆኖ መስራት እንደሚቻል የሚያሳይ መሆኑን አውስተዋል። የምርምር ሥራዎች መነሻም ሆነ መድረሻ የማኅበረሰብን ሕይወት መቀየር ነው ያሉት / ተክሉ የዚህ ምርምር ፕሮጀክት መሰራት እንደ ሀገርም ሆነ እንደ ክልል ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ የሚያስገኝ መሆኑን ተናግረዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብሔረሰቦች /ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ አዳማ ትንባዬ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል 32 ብሔረሰቦች በጋራ የሚኖሩበት ሕብረ ብሔራዊ ክልል መሆኑን ገልጸው ክልሉን የሰላም፣ የመቻቻልና የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ የክልሉ መንግስት በትኩረት እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የህብረተሰቡን ቋንቋና ባህል በማጥናት በውስጡ ያሉትን ሀገር በቀል ዕውቀቶች ለመሰነድ በክልሉ የሚገኙ አራት ዩኒቨርሲቲዎች ፕሮጀክት ይፋ ማድረጋቸው የሚበረታትና የሚያስመሰግናቸው መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ እንደ ክልል የበርካታ ብዝሃ ማንነት ባለቤቶች ነን ያሉት አቶ አዳማ የክልሉ ብሔረሰቦች /ቤት በክልሉ የሚገኙ ሀገር በቀል ዕውቀቶችን ለመሰነድ ለተጀመረው የምርምር ፕሮጀክት አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል፡፡

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ባህልና ስፖርት ቢሮ /ኃላፊና የቢሮ ኃላፊ ተወካይ አቶ ታሪኩ ኦይቻ ሀገር በቀል ዕውቀቶችን የማጥናት፣ የመሰነድና የማልማት ጉዳይ እንደ ክልል ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ መሆኑን ተናግረው ዩኒቨርሲቲዎች ሀገር በቀል ዕውቀቶችን በማጥናትና በመሰነድ ረገድ መስራታቸው የሚበረታታና ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሀገር በቀል ዕውቀቶችን በመሰነድና ከመጥፋት ለማዳን የጀመራቸው የምርምር ሥራዎች በእጅጉ የሚበረታቱ እንዲሁም ዘርፈ ብዙ ሀገራዊ ጠቀሜታ ያላቸው መሆኑን የገለጹት /ቢሮ ኃላፊው ቢሮው በመስኩ ላይ ለሚሰሩ የትብብር ምርምር ሥራዎች አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ቃል ገብተዋል፡፡

የዲላ ዩኒቨርሲቲ ምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር /ፕሬዝደንት / ሀብታሙ ተመስገን በበኩላቸው አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በተለይ 5 ተናጋሪዎች ብቻ የቀሩትን የኣንጎታ ቋንቋ እንዳይጠፋ እየሰራ የሚገኘው ሥራ የሚደንቅና የሚያስመስግን ትልቅ ሥራ መሆኑን ተናግረዋል። ጥንታዊትና የሰው ዘር መገኛ የሆነችው ኢትዮጵያ የበርካታ ሀገር በቀል ዕውቀቶችና ፍልስፍናዎች ባለቤት መሆኗን የሚናገሩት /ፕሬዝደንቱ በዚህ ረገድ በአራቱ ዩኒቨርሲቲዎች ትብብር ሀገር በቀል ዕውቀቶችን ለመሰነድ የተጀመረው ፕሮጀክት ለብዙ ነገር ግብአት ሆኖ የሚያገለግል ነው ብለዋል።

በመርሐ ግብሩ የኦንጎታ እና ኩየጉ ቋንቋዎችንና የማኅበረሰቡን ሀገር በቀል ዕውቀቶችን መሰነድን ትኩረት የደረጉት የምርምር ሥራዎች ውጤት፣ የደረሱበት ደረጃ፣ ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችና ምክረ ሃሳቦች በኘሮጀክቶቹ ዋና ተመራማሪዎች / ስንታየሁ ሰሙ እና / ዳኜ ማቼ ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

በተጨማሪም  በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሚገኙ ሀገር በቀል ዕውቀቶችን ለመሰነድ በሚከናወነው ፕሮጀክት ዙሪያ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በኩል የፕሮጀክቱ ዋና ተመራማሪ በሆኑት አቶ ካንስቴ ገሌቦ ገለጻ የቀረበ ሲሆን በገለጻቸው አራቱ ዩኒቨርሲቲዎች ባሉበት አካባቢ /Catchment Area/ የሚገኙ ሕዝቦችን ሀገር በቀል ዕውቀትን የመለየትና የመሰነድ ሥራ እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡ በዚህም መሠረት አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በጋሞ፣ ኮንሶ፣ ጋርዱላ እና አሌ ዞኖች የሚገኙ ዘጠኝ ብሔረሰቦች ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራ ሲሆን ዩኒቨርሲቲው ለሥራው ማስፈጸሚያ 1.75 ሚሊየን ብር መመደቡንና ከተለያዩ የትምህርት ዘርፎች የተወጣጣ የተመራማሪዎች ቡድን ማቋቋሙን ገልጸዋል።

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlV

የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ /ቤት