የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ስቴም (STEM) ማስተባበሪያ ማዕከል ከጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ፣ ጋርዱላና ኮሬ ዞኖች የተሻለ የትምህርትና የፈጠራ አቅም ያላቸውን 152 ተማሪዎች በመመልመል ለ45 ቀናት በተግባር የታገዘ ሥልጠና ሰጥቶ ነሐሴ 30/2016 ዓ/ም ሸኝቷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

የማኅበረሰብ ጉድኝትና የዩኒቨርሲቲ-ኢንደስትሪ ትስስር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ቶሌራ ሴዳ ተማሪዎቹ ሁለት ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ሠልጥነው ያሳዩት የፈጠራ ሥራ የሚደነቅ መሆኑን ገልጸው ፕሮጀክቱን ለማሳደግና ማዕከሉ እያከናወነ ያለውን ሥራ ለማጠናከር ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን መወጣት እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው የስቴም ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ ዶ/ር ብንያም ወንዳለ በአካባቢያቸው ባሉ ትምህርት ቤቶች የተሟሉ ላቦራቶሪዎች ለሌላቸው ከ7-12 ክፍል ተማሪዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ በተግባር የታገዘ ሥልጠና በመስጠት የፈጠራ አቅማቸውን እንዲያወጡ ለማስቻል የታለመ ፕሮጀክት መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ኃላፊው በ2016 ዓ/ም በማዕከሉ የተከናወኑ ተግባራትን የሚዳስስ ሪፖርት አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል፡፡

በፕሮግራሙ ማጠቃለያ ሥልጠናውን ተከታትለው ላጠናቀቁ ተማሪዎች የምስክር ወረቀት ተበርክቷል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ

የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCAD/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት