የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የኢንተርፕርነርሽፕ ልማትና ማበልፀጊያ ማዕከል በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ11ኛ ጊዜ ከኀዳር 9 - 15/2017 ዓ.ም የሚከበረውን የኢንተርፕርነርሽፕ ሳምንት ምክንያት በማድረግ በዩኒቨርሲቲያችን ለ3ኛ ጊዜ ተማሪዎችን ባሳተፈ ሁኔታ የቢዝነስ ዕቅድ ውድድር እና የኢንተርፕርነርሽፕ ሥልጠና በሁሉም ግቢዎች እያከናወነ ይገኛል፡፡ 

ስለሆነም ቅዳሜ በቀን 07/03/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡3ዐ ጀምሮ የሚሰጥ የአንድ ቀን ኢንተርኘርነርሽኘ ሥልጠና ስለተዘጋጀ በሥልጠናው ላይ እንድትሳተፉ ለሁሉም ተማሪዎች ጥሪ እናቀርባለን፡፡ ሥልጠናውን በተገቢው ሁኔታ ለሚከታተሉ ደረጃውን የጠበቀ ሰርትፊኬት የሚሰጥ ይሆናል፡፡


                  የሥልጠና አዳራሽ
ተ.ቁ              ግቢ                      አዳራሽ
1.        ዋና ግቢ                    አዲሱ አዳራሽ ከዋናው በር አጠገብ
2.        ጫሞ ካምፖስ            ዲ.ኤስ.ቲቪ አዳራሽ
3.        ሳውላ ካምፖስ           ዲ.ኤስ.ቲቪ አዳራሽ
4.        ኩልፎ ካምፖስ           ዲ.ኤስ.ቲቪ አዳራሽ
5.        አባያ  ካምፖስ           ዲ.ኤስ.ቲቪ አዳራሽ
6.        ነጭ ሳር ካምፖስ        ዲ.ኤስ.ቲቪ አዳራሽ


የአ/ም/ዩ ኢንተርፕርነርሽፕ ልማት እና ማበልፀጊያ ማዕከል

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCCD/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት