አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በሀገር አቀፍ ደረጃ አንጋፋና ገናና ስም ያለው በሀገራችን ከሚገኙ የመጀመሪያ ትውልድ ዩኒቨርሲቲዎች መካከል አንዱ ነው። ይህ እንዲሆን ለማስቻል መላው የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብና በየደረጃው ያሉ አመራሮች ሚና ወሳኝ ድርሻ አለው ብለን እናምናለን፡፡
የዩኒቨርሲቲያችን የቀድሞ አመራሮች ዩኒቨርሲቲው በመማር ማስተማር ሂደት ከፍተኛውን ደረጃ እንዲይዝ ብሎም በሀገሪቱ ካሉት ዩኒቨርሲቲዎች ሰላሙ የተጠበቀና ለሀገሪቱ የሰላም አምባሳደር ምልክት መሆን እንዲችል ላደረጋችሁት አስተዋጽኦ ኅብረቱ ምስጋናውን ያቀርባል፡፡ ከዚህም ባሻገር ኅብረቱን በሙሉ አቅማችሁ በመደገፍና ለተማሪዎች ምቹ ሁኔታ እንዲፈጠር ከኅብረቱ ጋር ተቀራርቦ በመሥራት ላሳያችሁን ትብብር ላቅ ያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡
አዲስ የተመደባችሁ የዩኒቨርሲቲያችን ከፍተኛ አመራሮች አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲን የመሰለ ግዙፍና አንጋፋ ተቋም ለመምራት ስለበቃችሁ እንኳን ደስ አላችሁ እያልን እንደ ተማሪዎች ኅብረት አደረጃጀት እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ ለሥራችሁ ምርኩዝ እና ለተግባራችሁ መደላድል ለመፍጠር የሚጠበቅብንን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ መሆናችንን እናረጋግጣለን።
በተለይም በአሁኑ ሰዓት አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ወደ ራስ ገዝነት ለሚያደርገው ሽግግር የሁሉም ባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ወሳኝ በመሆኑ ኅብረቱ ከትናንት በተሻለ ትጋት፤ ከአምናው በበለጠ ጥረት ኃላፊነታችንን ለመወጣት እንዲሁም ከዩኒቨርሲቲው አመራር የተሰጠንን ተልእኮ ለመተግበርና ከተማሪዎች የሚነሱ ሃሳቦችን ለማስፈጸም ዝግጁ መሆናችንን እናሳውቃለን፡፡
አዲስ ለተመደባችሁ የዩኒቨርሲቲያችን ከፍተኛ አመራሮች መልካም የሥራ ጊዜ እንዲሆንላችሁ እንመኛለን፡፡
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ኅብረት
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-
ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA
የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት