የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ኅብረት ኅብረቱን በተለያየ ኮሚቴና የኃላፊነት ደረጃ ላገለገሉ ተመራቂ ተማሪዎች ሽኝትና የዕውቅና መርሐ ግብር ሴኔ 17/2017 ዓ.ም አካሂዷል፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ዶ/ር ኢ/ር አብደላ ከማል የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ኅብረት ከዩኒቨርሲቲው አመራርና ማኅበረሰብ ጎን በመሆን የመማር ማስተማር ሥራን ጨምሮ ሌሎች የዩኒቨርሲቲው ተግባራት በተሳካ ሁኔታ እንዲፈጸሙ የበኩሉን ድርሻ ሲወጣ ቆይቷል ብለዋል፡፡ ምሩቅ የኅብረቱ አባላት በቀጣይ የተሳካ ጊዜ እንዲገጥማቸው ምኞታቸውን የገለጹት ፕሬዝደንቱ በቀጣይ የዩኒቨርሲቲው አልሙናይ በመሆን ከዩኒቨርሲቲው ጋር ያላቸው ግንኙነት እንዳይቋረጥ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
የተማሪዎች ኅብረት ፕሬዝደንት ተማሪ ሶፎኒያስ ፈንቴ በስድስቱም የዩኒቨርሲቲው ካምፓሶች በተለያየ የኃላፊነት ደረጃ ሲያገለግሉ የቆዩ ተመራቂ ተማሪዎች በሥራ ቆይታቸው ለባረከቱት አተዋጽኦ በኅብረቱ ስም ምስጋናውን አቅርቧል፡፡ የሽኝትና መስጋና መርሐ ግብሩም አባላቱ ለኅብረቱ ሥራ መሳካት ላበረከቱት አስተዋጽኦ ዕውቅና ለመስጠት የተዘጋጀ መሆኑን ጠቁሟል፡፡
ኅብረቱን በምክትል ፕሬዝደንትነት ያገለገለችው ተመራቂ ተማሪ አፀደ ጌትነት በተደረገው ሽኝትና ዕውቅና በእጅጉ መደሰቷን ገልጻ በኅብረቱ በነበራት የሥራ ላይ ቆይታ የአመራርነት፣ የተግባቦትና በራስ የመተማመን አቅሟን እንድታዳብር የረዳት መሆኑን ገልጻለች፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-
ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA
የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት