የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ነባር የ2015 እና የ2016 ባች ቅድመ ምረቃ መደበኛ ፕሮግራም ተማሪዎች መግቢያ ቀን እሁድ መስከረም 5/2017 ዓ.ም እንዲሆን ተወስኗል፡፡


በዚህ መሠረት የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ነባር የ2015 እና የ2016 ባች ቅድመ ምረቃ መደበኛ ፕሮግራም ተማሪዎች እሁድ መስከረም 5/2017 ዓ.ም በየካምፓሶቻችሁ እንድትገኙ እያሳሰብን ሰኞ መስከረም 6/2017 ዓ.ም ከዚህ ቀደም በሀገራዊ ፕሮግራሞች መደራረብ ምክንያት ተቋርጦ የነበረው ትምህርትና ፈተና የሚሰጥ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ማሳሰቢያ፡- ከተጠቀሰው ቀን ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣ ተማሪን ዩኒቨርሲቲው አያስተናግድም፡፡

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሬጂስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት