የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ነባር የክረምት መርሃ ግብር ተማሪዎች እና በ2016 ክረምት ለሚሰጠው ልዩ የመምህራንና ትምህርት አመራሮች አቅም ማጎልበቻ ሥልጠና አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ መምህራንና ትምህርት አመራሮች መግቢያ እንደሚከተለው እንዲሆን ተወስኗል፡፡
1ኛ) የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ነባር የክረምት መርሃ ግብር ተማሪዎች መግቢያ ቀን እሁድ ሐምሌ 21 ቀን 2016 ዓ.ም፣ ምዝገባ የሚፈጸመው ሐምሌ 22 ቀን 2016 ዓ.ም፣ ትምህርት የሚጀመረዉ ማክሰኞ ሐምሌ 23 ቀን 2016 ዓ.ም ሆኖ የመግቢያና የመማሪያ ካምፓስን በተመለከተ የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎች አባያ ካምፓስ፣ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት፣ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ፣ የማኅበራዊ ሳይንስና ሥነ ሰብ ኮሌጅ፣ የህግ ትምህርት ቤት እና የሥነ ትምህርትና ሥነ ባህርይ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በአጠቃላይ ዋናው ግቢ እና የሳውላ ካምፓስ ተማሪዎች ሳውላ ካምፓስ፤
2ኛ) በ2016 ክረምት ለሚሰጠው ልዩ የመምህራንና የትምህርት አመራሮች አቅም ማጎልበቻ ሥልጠና አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ መምህራንና ትምህርት አመራሮች መግቢያ ሰኞ ሐምሌ 22 ቀን 2016 ዓ.ም ሆኖ የመግቢያና ሥልጠና ቦታ ጫሞ ካምፓስ፤
መሆኑን እየገለጽን ነባር የክረምት መርሃ ግብር ተማሪዎችም ሆነ ልዩ የአቅም ማጎልበቻ ሠልጠኞች ወደ ዩኒቨርሲቲው በምትመጡበት ጊዜ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ ይዛችሁ እንድትመጡ ዩኒቨርሲቲው ያሳውቃል፡፡
ማሳሰቢያ፡- ከተጠቀሰው ቀን ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣ ተማሪንም ሆነ ልዩ ሠልጣኝ ዩኒቨርሲቲው የማያስተናግድ መሆኑን በጥብቅ ያሳውቃል፡፡
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሬጂስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-
ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCAD/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA
የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት